ዘፍጥረት 24:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሰውየው ወደ ቤት ሄደ፤ ላባም በግመሎቹ ላይ የነበረውን ጭነት አራግፎ ገለባና ድርቆሽ አቀረበላቸው፤ ቀጥሎም የአብርሃም አገልጋይና አብረውት የነበሩት ሰዎች እግራቸውን የሚታጠቡበት ውሃ አመጣላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውየው ከላባ ጋራ ወደ ቤት ሄደ፤ የግመሎቹ ጭነት ተራግፎ ገለባና ድርቈሽ ተሰጣቸው፤ ለርሱና ዐብረውት ለነበሩት ሰዎች የእግር ውሃ ቀረበላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውዬውም ወደ ቤት ገባ፥ ግመሎቹንም አራገፈ፥ ገለባና ገፈራም ለግመሎቹ አቀረበ፥ እግሩን ይታጠብ ዘንድ፥ ከእርሱም ጋር ላሉት ሰዎች እግር ውኃ አቀረበ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውዬውም ወደ ቤት ገባ፤ ግመሎቹንም አራገፈ፤ ለግመሎቹም ሣርና ገለባ አቀረቡላቸው፤ እግሩን ይታጠብ ዘንድ ውኃ አመጡለት፤ ከእርሱ ጋር ላሉ ሰዎችም አመጡላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውዮውም ወደ ቤት ገባ ግመሎቹንም አራገፈ ገለባና ገፈራም ለግመሎቹ አቀረበ፤ እግሩን ይታጠብ ዘንድ ከእርሱም ጋር ላሉት ሰዎች እግር ውኃ አቀረበ። |
“ጌቶቼ ሆይ፥ ተቀብዬ ላስተናግዳችሁ ዝግጁ ነኝ፤ እባካችሁ ወደ ቤቴ ግቡ፤ እግራችሁንም ታጥባችሁ እዚሁ ዕደሩ፤ ጠዋት በማለዳ ተነሥታችሁ ጒዞአችሁን ትቀጥላላችሁ” አላቸው። እነርሱ ግን “አይሆንም፤ እኛ እዚሁ በከተማይቱ አደባባይ እናድራለን” አሉት።
ላባም የእኅቱ ልጅ ያዕቆብ መምጣቱን በሰማ ጊዜ ሊቀበለው ፈጥኖ ሄደ፤ ዐቅፎ ከሳመውም በኋላ ወደ ቤት አመጣው፤ ያዕቆብ የሆነውን ሁሉ ለላባ ነገረው፤
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ሴትዮዋ መለስ ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ “ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ስገባ አንተ ውሃ እንኳ ለእግሬ አላቀረብክልኝም፤ እርስዋ ግን እግሬን በእንባዋ አጥባ በጠጒርዋ አበሰችው።
እንዲሁም ልጆችን በሚገባ በማሳደግ፥ እንግዳን በመቀበል፥ የቅዱሳንን እግር በማጠብ፥ የተቸገሩትን በመርዳትና ማንኛውንም በጎ ሥራ ሁሉ በማከናወን ለመልካም ሥራም ሁሉ የተጋች መሆን አለባት።