ዘፍጥረት 23:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የሒታውያን የነበረው እርሻ በውስጡ ካለው ዋሻ ጋር የአብርሃም የመቃብር ርስት ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ዕርሻውና ውስጡ የሚገኘው ዋሻ የመቃብር ቦታ እንዲሆን ከኬጢያውያን ለአብርሃም በርስትነት ተላለፈለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሻውና በእርሱ ያለው ዋሻው በሒታውያን ልጆች ዘንድ ለአብርሃም የመቃብር ርስት ሆኖ ጸና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሻውና በእርሱ ያለው ዋሻም በኬጢ ልጆች ዘንድ ለአብርሃም የመቃብር ርስት ሆኖ ጸና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሻውና በእርሱ ያለው ዋሻው በኬጢ ልጆች ዘንድ ለአብርሃም የመቃብር ርስት ሆኖ ጸና። |
ልጆቹ ይስሐቅና እስማኤል ማክፌላ በተባለ ዋሻ ቀበሩት፤ ይህም ዋሻ ከመምሬ በስተምሥራቅ በሒታዊው በጾሐር ልጅ በዔፍሮን እርሻ ውስጥ የሚገኘው ነው፤
ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ልጆቹን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፤ “እኔ በሞት ወደ ወገኖቼ የምሄድበት ጊዜ ደርሶአል፤ ስለዚህ በሒታዊው በዔፍሮን እርሻ ላይ ባለው ዋሻ ውስጥ ከአባቶቼ ጋር ቅበሩኝ፤
አስከሬኑን ወደ ከነዓን ወስደው ከመምሬ በስተምሥራቅ በምትገኘው በማክፌላ ዋሻ ቀበሩት፤ ይህም ዋሻ አብርሃም ለመቃብር ቦታ እንዲሆን ከሒታዊው ከዔፍሮን በገዛው እርሻ ውስጥ የሚገኝ ነው።
‘አባቴ ለመሞት ሲቃረብ በከነዓን ምድር ባዘጋጀው መቃብር እንድቀብረው በመሐላ ቃል አስገብቶኛል፤ ስለዚህ እዚያ ሄጄ አባቴን ቀብሬ እንድመለስ ይፈቀድልኝ ሲል ጠይቆአል’ ብላችሁ ንገሩልኝ” አላቸው።
ንጉሥ ዳዊት ግን “ይህስ አይሆንም፤ ዋጋውን መክፈል አለብኝ፤ እኔ ምንም ዋጋ ያላወጣሁበትን ነገር ለአምላኬ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጌ ማቅረብ አይገባኝም” አለው፤ ከዚህም በኋላ ዳዊት አውድማውንና በሬዎቹን በኀምሳ ጥሬ ብር ገዛ፤