“ጌታዬ የመሬቱ ዋጋ አራት መቶ ብር ቢሆን ነው፤ ታዲያ ይህ በእኔና በእናንተ መካከል ምንድን ነው? ይልቅስ የሚስትህን አስከሬን እዚህ ቅበር።”
ዘፍጥረት 23:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብርሃምም በነገሩ ተስማምቶ ዔፍሮን በሕዝቡ ፊት በተናገረው መሠረት በነጋዴዎች ሚዛን ልክ አራት መቶ ብር መዝኖ ሰጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብርሃምም፣ ኤፍሮን በኬጢያውያን ፊት በተናገረው ዋጋ ተስማማ፤ በወቅቱም የንግድ መለኪያ መሠረት አራት መቶ ጥሬ ብር መዘነለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃምም ከኤፍሮን ጋር ተስማማ፥ በሒታውያንም ልጆች ፊት የነገረውን አራት መቶ ሰቅል በነጋዴዎች ሚዛን ልክ መዝኖ አብርሃም ለኤፍሮን ሰጠው፥ ብሩም ለመሸጫ ለመለወጫ የሚተላለፍ ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም የኤፍሮንን ነገር ሰማ፤ አብርሃምም በኬጢ ልጆች ፊት የነገረውንና ተቀባይነት ያለውን ግብዝ ያይደለ አራት መቶ ምዝምዝ ብር መዝኖ ለኤፍሮን ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምም የኤፍሮንን ነገር ሰማ አብርሃምም በኬጢ ልጆች ፊት የነገረውን አራት መቶ ሰቅል መዝኖ ለኤፍሮን ሰጠው ብሩም ለመሸጫ ለመለወጫ የሚተላለፍ ነበረ። |
“ጌታዬ የመሬቱ ዋጋ አራት መቶ ብር ቢሆን ነው፤ ታዲያ ይህ በእኔና በእናንተ መካከል ምንድን ነው? ይልቅስ የሚስትህን አስከሬን እዚህ ቅበር።”
ስንመለስ በመንገድ ለዐዳር በሰፈርንበት ቦታ ስልቻዎቻችንን ስንፈታ የያንዳንዳችንን ገንዘብ ምንም ሳይጐድልለት በየስልቻዎቻችን አፍ ላይ ተቋጥሮ አገኘነው። እነሆ፥ ያንን ገንዘብ መልሰን አምጥተናል።
ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ልጆቹን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፤ “እኔ በሞት ወደ ወገኖቼ የምሄድበት ጊዜ ደርሶአል፤ ስለዚህ በሒታዊው በዔፍሮን እርሻ ላይ ባለው ዋሻ ውስጥ ከአባቶቼ ጋር ቅበሩኝ፤
አስከሬኑን ወደ ከነዓን ወስደው ከመምሬ በስተምሥራቅ በምትገኘው በማክፌላ ዋሻ ቀበሩት፤ ይህም ዋሻ አብርሃም ለመቃብር ቦታ እንዲሆን ከሒታዊው ከዔፍሮን በገዛው እርሻ ውስጥ የሚገኝ ነው።
የራሱ ጠጒር እጅግ ብዙ ነበር፤ ስለሚረዝምበትና ስለሚከብደው በዓመት አንድ ጊዜ ይቈርጠው ነበር፤ የጠጒሩም ክብደት በቤተ መንግሥት ሚዛን ሲለካ ከሁለት ኪሎ በላይ ነበር።
ንጉሥ ዳዊት ግን “ይህስ አይሆንም፤ ዋጋውን መክፈል አለብኝ፤ እኔ ምንም ዋጋ ያላወጣሁበትን ነገር ለአምላኬ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጌ ማቅረብ አይገባኝም” አለው፤ ከዚህም በኋላ ዳዊት አውድማውንና በሬዎቹን በኀምሳ ጥሬ ብር ገዛ፤
ከሕዝብ ቈጠራ ውስጥ የሚገባ እያንዳንዱ ሰው በተቀደሰው ድንኳን በታወቀው ሚዛን ልክ አንድ ጥሬ ብር ይክፈል፤ እያንዳንዱ ሰው ይህን ለእግዚአብሔር መባ አድርጎ ያቅርብ፤
እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ሁሉ፥ እናንተም ለእነርሱ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ የሕግና የነቢያት ትምህርትም የሚሉት ይህንኑ ነው።
አእምሮአችሁ በእነዚህ ከሁሉ በሚበልጡና በሚያስመሰግኑ መልካም ነገሮች የተመላ ይሁን፤ በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ! እውነተኛ፥ ክቡር፥ ትክክለኛ፥ ንጹሕ፥ አስደሳችና ምስጉን የሆኑ ነገሮችን ሁሉ አስቡ።
በዚህ ነገር ማንም ሰው አይተላለፍ፤ ሌላ አማኝን አይበድል፤ ከዚህ በፊት እንደ ነገርናችሁና እንዳስጠነቀቅናችሁ እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉትን ጌታ ይቀጣቸዋል።