ዘፍጥረት 21:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ አቤሜሌክ ከሠራዊቱ አለቃ ከፊኮል ጋር ሄደና አብርሃምን “በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ አቢሜሌክ ከሰራዊቱ አለቃ ከፊኮል ጋራ ሆኖ አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “በምታደርገው ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ዘመን አቢሜሌክ ከሙሽራው ወዳጅ ከአኮዘትና ከሠራዊቱ አለቃ ከፊኮል ጋር አብርሃምን አለው፦ “በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ዘመን አቤሜሌክ፥ ሚዜው አኮዘትና የሠራዊቱ አለቃ ፋኮል ወደ አብርሃም ሄደው አሉት፥ “በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ዘመን አቢሜሌክ ከሙሽራው ወዳጅ ከአኮዘትና ከሠራዊቱ አለቃ ከፊኮል ጋር አብርሃምን አለው፤ በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤ |
ከዚያ በኋላ አብርሃም ለእግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም አቤሜሌክንና ሚስቱን፥ ሴቶች አገልጋዮቹንም ፈውሶአቸው ልጆች እንዲወልዱ አድርጎአቸዋል፤
እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “እግዚአብሔር ከአንተ ጋር መሆኑን በግልጥ ዐውቀናል፤ ስለዚህ በእኛና በአንተ መካከል በሰላም ለመኖር የሚያስችል ስምምነት በመሐላ ለመፈጸም አስበናል፤ በዚህም መሠረት ቃል ኪዳን እንድትገባልን የምንፈልገው፥
አይዞህ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ በምትሄድበትም ስፍራ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚህም ምድር በደኅና እመልስሃለሁ፤ የገባሁልህን ቃል ኪዳን ሁሉ እፈጽምልሃለሁ፤ ከቶም አልተውህም።”
ቀጥሎም በደቡብ በኩል ወደተመሸገችው ወደ ጢሮስ ከተማና እንዲሁም ወደ ሒዋውያንና ወደ ከነዓናውያን ከተሞች ሁሉ ሄዱ፤ በመጨረሻም በይሁዳ ወደምትገኘው ወደ ቤርሳቤህ ዘለቁ፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የግብጽ ሀብትና የኢትዮጵያ ሸቀጥ ለእናንተ ተላልፎ ይሰጣል፤ ቁመታቸው ረጃጅም የሆነ የሳባ ሰዎችም በሰንሰለት ታስረው በመምጣት ይከተሉአችኋል፤ እጅ ነሥተውም፦ ‘እግዚአብሔር የሚገኘው በእናንተ ዘንድ ብቻ ነው፤ በሌላ አይደለም፤ ከእርሱም በቀር ሌላ አምላክ የለም’ ይላሉ።”
የጦር ዕቅድንም አውጡ፤ ነገር ግን እናንተ እንዳሰባችሁት አይሳካላችሁም፤ የፈለጋችሁትን ያኽል ተናገሩ፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለ ሆነ ምክራችሁ አይጸናም።
በእነዚያ ቀኖች ዐሥር የሌላ አገር ሰዎች ወደ አንድ አይሁዳዊ ቀርበው የልብሱን ዘርፍ በመያዝ ‘እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር መሆኑን ስለ ሰማን ከእናንተ ጋር እንሂድ’ ይሉታል።”
“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙም ‘ዐማኑኤል’ ተብሎ ይጠራል።” ዐማኑኤል ማለትም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው” ማለት ነው።
እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “ከሙሴ ጋር እንደ ነበርኩ ከአንተም ጋር የምሆን መሆኔን ያውቁ ዘንድ እኔ ዛሬ በእስራኤላውያን ሁሉ ፊት አንተን ከፍ፥ ከፍ ማድረግ እጀምራለሁ።
እንግዲህ፥ አይሁድ ሳይሆኑ አይሁድ ነን የሚሉትን እነዚያን ከሰይጣን ማኅበር የሆኑትን ውሸታሞች መጥተው በእግርህ ሥር እንዲወድቁ አደርጋቸዋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኩህም እንዲያውቁ አደርጋቸዋለሁ።