ዘፍጥረት 20:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም እርስዋ የአባቴ ልጅ ስለ ሆነች በእርግጥ እኅቴ ናት፤ ነገር ግን የእናቴ ልጅ ስላልሆነች አገባኋት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም እኮ በርግጥ እኅቴ ናት፤ ከአንድ እናት ባንወለድም በአባት አንድ ነን፤ ኋላም አገባኋት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ደግሞ በእውነት እኅቴ ናት፥ የእናቴ ልጅ አይደለችም እንጂ የአባቴ ልጅ ናት፥ ለእኔም ሚስት ሆነች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም ደግሞ በእናቴ ወገን አይደለችም እንጂ በእውነት በአባቴ ወገን እኅቴ ናት፤ ለእኔም ሚስት ሆነች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም ደግሞ በእውነት እኅቴ ናት የእናቴ ልጅ አይደለችም እንጂ የአባቴ ልጅ ናት ለእኔም ሚስት ሆነች። |
አብርሃምም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ ‘እዚህ ቦታ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው የለም’ ብዬ በማሰብ ‘ሚስቴን ለመውሰድ በመፈለግ ይገድሉኛል’ ብዬ ስለ ሰጋሁ ነው፤
ስለዚህ እግዚአብሔር ከአባቴ ቤት ወጥቼ ወደ ባዕድ አገር እንድሄድ ባዘዘኝ ጊዜ ‘በምንሄድበት ቦታ ሁሉ እኅቱ ነኝ ብትዪ ለእኔ ታላቅ ውለታ እንዳደረግሽልኝ እቈጥረዋለሁ’ ብዬአት ነበር።”
የዚያ አገር ሰዎችም ስለ ርብቃ “ምንህ ናት” ብለው በጠየቁት ጊዜ “እኅቴ ናት” አላቸው፤ ይህንንም ያለበት ምክንያት ርብቃ በጣም ቈንጆ ስለ ነበረች የዚያ አገር ሰዎች በእርስዋ ሰበብ እንዳይገድሉት በመፍራት ነው።
እንደዚህ ካዋረድከኝ በኋላ በሕዝብ ፊት ራሴን ቀና አድርጌ ለመሄድ እንዴት እችላለሁ? አንተም ብትሆን በእስራኤል እጅግ የተዋረድክ ትሆናለህ፤ ይልቅስ ለንጉሡ ብትነግረው እኔን ለአንተ በሚስትነት እንደሚሰጥህ እርግጠኛ ነኝ” አለችው።