ዘፍጥረት 2:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሦስተኛው ወንዝ ጤግሮስ ይባላል፤ እርሱም በአሦር በስተምሥራቅ ይፈስሳል፤ አራተኛው ወንዝ ኤፍራጥስ ይባላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሦስተኛው፣ ከአሦር በስተምሥራቅ የሚፈስሰው የጤግሮስ ወንዝ ሲሆን፣ አራተኛው የኤፍራጥስ ወንዝ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሦስተኛውም ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው፥ እርሱም በአሦር ምሥራቅ የሚሄድ ነው። አራተኛውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሦስተኛውም ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው፤ እርሱም በአሶር ላይ የሚሄድ ነው። አራተኛውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሦስተኚውም ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው፤ እርሱም በአሦር ምሥራቅ የሚሄድ ነው። |
በዚያን ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ በማለት ቃል ኪዳን ገባለት፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ሁሉ ለዘሮችህ እሰጣለሁ፤
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ሰውን በዔደን የአትክልት ቦታ አኖረው፤ ይህንንም ያደረገው ሰው የአትክልቱን ቦታ እንዲያለማና እንዲንከባከበው ነው።
የእስማኤል ዘሮች ከግብጽ በስተምሥራቅ ወደ አሦር በምትወስደው መንገድ በሐዊላና በሹር መካከል ይኖሩ ነበር፤ የኖሩትም ከሌሎቹ የአብርሃም ዘሮች ጋር በጥላቻ ተራርቀው ነበር።
ባቢሎናውያንንና ከለዳውያንን ሁሉ አመጣለሁ፤ የፈቆድን፥ የሾዐንና የቆዐንን ወንዶች እንዲሁም አሦራውያንን ሁሉ አመጣለሁ፤ ወጣትነት ያላቸው፥ መልከ ቀና የሆኑ መሳፍንትና የጦር መኰንኖች፥ ታላላቅ ባለሥልጣኖችና ከፍተኛ ማዕርግ ያላቸው እነዚህ ሁሉ በፈረስ ተቀምጠው ይመጣሉ።
ሰፈራችሁን ነቅላችሁ ወደ ተራራማው የአሞራውያን አገር፥ ወደ ጐረቤትም ወደ አራባ በደጋውና በቈላው አገር፥ በኔጌብ፥ በሜዲቴራኒያን ባሕር ጠረፍ በኩል፥ በከነዓናውያን አገርና በሊባኖስ በኩል አድርጋችሁ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ ሂዱ።
ስታልፉ በእግራችሁ የምትረግጡት መሬት ሁሉ የእናንተ ይሆናል፤ ግዛታችሁም በደቡብ በኩል ካለው በረሓ ተነሥቶ በሰሜን በኩል እስካሉት እስከ ሊባኖስ ተራራዎች፥ እንዲሁም በምሥራቅ በኩል ከሚገኘው ከኤፍራጥስ ወንዝ ተነሥቶ በምዕራብ በኩል እስከሚገኘው እስከ ታላቁ ሜዲቴራኒያን ባሕር ድረስ ይሰፋል።