Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 2:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የሦስተኛውም ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው፥ እርሱም በአሦር ምሥራቅ የሚሄድ ነው። አራተኛውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ሦስተኛው፣ ከአሦር በስተምሥራቅ የሚፈስሰው የጤግሮስ ወንዝ ሲሆን፣ አራተኛው የኤፍራጥስ ወንዝ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ሦስተኛው ወንዝ ጤግሮስ ይባላል፤ እርሱም በአሦር በስተምሥራቅ ይፈስሳል፤ አራተኛው ወንዝ ኤፍራጥስ ይባላል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ወንዝ ስም ጤግ​ሮስ ነው፤ እር​ሱም በአ​ሶር ላይ የሚ​ሄድ ነው። አራ​ተ​ኛ​ውም ወንዝ ኤፍ​ራ​ጥስ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የሦስተኚውም ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው፤ እርሱም በአሦር ምሥራቅ የሚሄድ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 2:14
11 Referencias Cruzadas  

በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፥


እርሱም መለከት ለያዘው ስድስተኛው መልአክ “በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ የታሰሩትን አራቱን መላእክት ፍታቸው፤” አለው።


በእግራችሁ የምትረግጡት ስፍራ ሁሉ የእናንተ ይሆናል፤ ግዛታችሁም ከምድረ በዳው እስከ ሊባኖስ፥ ከኤፍራጥስ ወንዝ አንሥቶ በስተ ምዕራብ እስካለው ባሕር ይደርሳል።


ተመልሳችሁ ተጓዙ፥ ወደ ተራራማው ወደ አሞራውያን አገር፥ ወደ አጎራባቾቹም በዓረባም በደጋውና በቆላው ሁሉ፥ በኔጌብም በባሕርም ዳር ወዳሉ ከነዓናውያን ምድር፥ ወደ ሊባኖስም እስከ ታላቁ ወንዝም እስከ ኤፍራጥስ ድረስ ሂዱ።


ዘሮቹም ከግብጽ በስተ ምሥራቅ ወደ አሦር በምትወስደው መንገድ በሐዊላና በሹር መካከል ሲሰፍሩ፤ የኖረውም በወንድሞቹ ሁሉ ፊት በተቃርኖ ነበር።


የሴም ልጆች፦ ዔላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ እና አራም ናቸው።


ከዚያም ወደ አሦር ሄደና ነነዌን፥ ረሆቦትን፥ ካላሕን መሠረተ፤


የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፥ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል።


ጌታ እግዚአብሔርም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በዔደን ገነት አኖረው።


እነርሱም የባቢሎን ልጆች፥ ከለዳውያን ሁሉ ፋቁድ፥ ሾዓ፥ ቆዓ፥ ከእነርሱም ጋር የአሦር ልጆች ሁሉ፥ ሁሉም መልከ መልካም ወጣቶች፥ ገዢዎች፥ ባለ ሥልጣናት፥ መኰንኖችና የተጠሩ፥ ሁሉም ፈረስ የሚጋልቡ ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios