ሎጥ ዙሪያውን በተመለከተ ጊዜ የዮርዳኖስ ሸለቆ እስከ ጾዓር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነት ወይም እንደ ግብጽ ምድር ውሃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ ይህን የተመለከተው እግዚአብሔር የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ከማጥፋቱ በፊት ነበር።
ዘፍጥረት 19:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደዚያች ከተማ እስከምትደርስ ምንም ማድረግ ስለማልችል ፈጥነህ ወደ እርስዋ ሽሽ!” አለው። ሎጥ ያቺን ከተማ ትንሽ ብሎአት ስለ ነበር ጾዓር ተባለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ እዚያ እስክትደርስ ድረስ አንዳች ማድረግ ስለማልችል ቶሎ ብለህ ወደዚያ ሽሽ።” ስለዚህም የዚያች ከተማ ስም ዞዓር ተባለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቶሎ ወደዚያ ሸሽትህ አምልጥ፥ ወደዚያ እስክትደርስ ድረስ ምንም አደርግ ዘንድ አልችልምና።” ስለዚህም የዚያች ከተማ ስም ጾዓር ተባለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ፍጠንና በዚያ ራስህን አድን፤ ወደዚያ እስክትደርስ ድረስ ምንም አደርግ ዘንድ አልችልምና።” ስለዚህም የዚያች ከተማ ስም ሴጎር ተባለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቶሎ ወደዚያ ሸሽትህ አምልጥ ወደዚያ እስክትደርስ ድረስ ምንም አደርግ ዘንድ አልችልምና። ስለዚህም የዚያች ከተማ ስም ዞዓር ተባለ። |
ሎጥ ዙሪያውን በተመለከተ ጊዜ የዮርዳኖስ ሸለቆ እስከ ጾዓር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነት ወይም እንደ ግብጽ ምድር ውሃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ ይህን የተመለከተው እግዚአብሔር የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ከማጥፋቱ በፊት ነበር።
እነዚህ አራቱ ነገሥታት፥ ሌሎችን አምስት ነገሥታት ለመውጋት ሄዱ፤ የተዘመተባቸውም አምስት ነገሥታት የሰዶም ንጉሥ ቤራዕ፥ የገሞራ ንጉሥ ቢርሻዕ፥ የአዳማ ንጉሥ ሺንአብ፥ የጸቦይም ንጉሥ ሼሜቤርና ጾዓር ተብላ የምትጠራው የቤላዕ ንጉሥ ነበሩ።
ስለ ሞአብ ከልቤ አለቅሳለሁ፤ ሕዝቡ ወደ ጾዓርና ወደ ዔግላት ሸሊሺያ ኰበለሉ፤ ጥቂቶችም ወደ ሉሒት አቀበት ወጡ፤ በሚወጡበትም ጊዜ ያለቅሱ ነበር፤ ሌሎች ደግሞ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ስለ ጥፋታቸው እያለቀሱ ወደ ሖሮናይም ለማምለጥ ይሞክራሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ወይን ጠጅ ከወይን ዘለላ እንደሚገኝና ‘በረከት ስላለበት አታጥፉት’ እንደሚባል እኔም በዚሁ ዐይነት ስለ አገልጋዮቼ ስል ሕዝቡን በሙሉ አላጠፋም።
“የሐሴቦንና የዔልዓሌ ሕዝብ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይጮኻሉ፤ ጩኸታቸውም እስከ ያሀጽ ተሰምቶአል፤ ከጾዓር እስከ ሖሮናይምና ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ተሰምቶአል፤ የኒምሪም ውሃ እንኳ ደርቆአል።
እንግዲህ ተወኝ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ማንም ሊያስታውሳቸው በማይችል ሁኔታ ልደምስሳቸው፤ ከዚያም በኋላ አንተን ከእነርሱ ይበልጥ ኀይልና ብዛት ላለው ሕዝብ አባት አደርግሃለሁ።’