ዘፍጥረት 12:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ‘እኅቱ ነኝ’ በያቸው፤ በዚህ ዐይነት በአንቺ ምክንያት በሕይወት እንድኖር ይተዉኛል፤ በደኅና ዐይንም ይመለከቱኛል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ለአንቺ ሲሉ እንዲንከባከቡኝ፣ ሕይወቴም እንድትተርፍ፣ ‘እኅቱ ነኝ’ በዪ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ በአንቺ ምክንያት መልካም ይሆንልኝ ዘንድ፥ ስለ አንቺም ነፍሴ ትድን ዘንድ፦ እኅቱ ነኝ በዪ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ በአንቺ ምክንያት መልካም ይሆንልኝ ዘንድ፥ ስለ አንቺም ነፍሴ ትድን ዘንድ እኅቱ ነኝ በዪ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ በአንቺ ምክንያት መልካም ይሆንልኝ ዘንድ ስለ አንቺም ነፍሴ ትድን ዘንድ፥ እኅቱ ነኝ በዩ። |
እኅቴ ነች ያለኝ ራሱ አብርሃም ነው፤ እርስዋም ወንድሜ ነው ብላኛለች፤ እኔ ይህን ያደረግኹት በቅንነትና በንጹሕ ኅሊና ስለ ሆነ ምንም በደል አልፈጸምኩም” አለ።
የዚያ አገር ሰዎችም ስለ ርብቃ “ምንህ ናት” ብለው በጠየቁት ጊዜ “እኅቴ ናት” አላቸው፤ ይህንንም ያለበት ምክንያት ርብቃ በጣም ቈንጆ ስለ ነበረች የዚያ አገር ሰዎች በእርስዋ ሰበብ እንዳይገድሉት በመፍራት ነው።
“እኔን ባለማስታወስና ስለ እኔ ባለማሰብ ውሸት የተናገራችሁት ማንን ፈርታችሁ ነው? እኔን ያልፈራችሁኝ ለብዙ ጊዜ ዝም ስለልኩና እንዳላየ ስለሆንኩ ነውን?
ከዚህም በኋላ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስለ እርሱ ያለውን ሁሉ እንዲህ ብዬ ነገርኩት፦ “የባቢሎን ንጉሥ ለላካቸው ባለ ሥልጣኖች እጅህን ብትሰጥ ሕይወትህ ትተርፋለች፤ ይህችም ከተማ ከመቃጠል ትድናለች፤ አንተና ቤተሰብህም ሁሉ ከጥፋት ትድናላችሁ፤
እኔም እንዲህ አልኩት፦ “አይዞህ! ለእነርሱ ተላልፈህ አትሰጥም፤ እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል እንድትሰማ እለምንሃለሁ፤ ለአንተም መልካም ነገር ይሆንልሃል፤ ሕይወትህም ከጥፋት ትድናለች።
እናንተ የአባታችሁ የዲያብሎስ ልጆች ናችሁ፤ ፍላጎታችሁም የአባታችሁን ምኞት መፈጸም ነው፤ እርሱ ከመጀመሪያ አንሥቶ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነት በእርሱ ስለሌለ ከእውነት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤ እርሱ ሐሰተኛና የሐሰት ሁሉ አባት ስለ ሆነ ሐሰት በሚናገርበት ጊዜ ከገዛ ራሱ አውጥቶ ይናገራል።
ከኃጢአት የሚገኘው ዋጋ ሞት ነው፤ ከእግዚአብሔር የሚሰጠው ስጦታ ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የሚገኘው የዘለዓለም ሕይወት ነው።