ዘፍጥረት 11:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሰዎቹ ይሠሩአቸው የነበሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ግን ሰዎቹ ይሠሩ የነበሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም የሰዎች ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። |
እግዚአብሔር በእሳት ስለ ወረደበት መላው የሲና ተራራ በጢስ ተሞላ። ጢሱም ከእሳት ምድጃ እንደሚወጣ ዐይነት ሆኖ ወደ አየር ተትጐለጐለ፤ ሰዎቹም እጅግ ፈርተው ተንቀጠቀጡ።
እነርሱንም ከግብጻውያን እጅ ለማዳን ወርጃለሁ፤ ከግብጽም አውጥቼ አሁን ከነዓናውያን፥ ሒታውያን፥ አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን፥ የሚኖሩባትን፥ በማርና በወተት የበለጸገችውን ሰፊና ለም የሆነችውን ምድር እሰጣቸዋለሁ።
ከእግዚአብሔር ፊት የሚሰወር ምንም ፍጥረት የለም፤ በእርሱ ዐይን ፊት ሁሉ ነገር ግልጥና ዕርቃኑን ሆኖ የሚታይ ነው፤ እኛም መልስ መስጠት የሚገባን በእርሱ ፊት ነው።