ዘፍጥረት 10:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት የከነዓናውያን ድንበር ከሲዶና አንሥቶ በስተደቡብ በገራር አጠገብ እስካለው እስከ ጋዛ ድረስ፥ በስተ ምሥራቅ እስከ ሰዶም፥ ገሞራ፥ አዳማና በላሻዕ አጠገብ እስካለው እስከ ጸቦይም ድረስ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የከነዓን ወሰን ከሲዶና አንሥቶ በጌራራ በኩል እስከ ጋዛ ይደርሳል፤ ከዚያም በሰዶም በኩል ገሞራን፣ አዳማንና ስቦይን ይዞ እስከ ላሣ ይዘልቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ዓይነት የከነዓናውያን ድንበር ከሲዶና አንሥቶ፥ በገራር አጠገብ እስካለው እስከ ጋዛ ድረስ፥ ወደ ሰዶም እና ገሞራ፥ አዳማና በላሻዕ አጠገብ እስካለው እስከ ጸቦይም ድረስ ይደርሳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከነዓናውያንም ወሰን ከሲዶን እስከ ጌራራና ጋዛ ድረስ ነው፤ ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ፥ ወደ አዳማና ወደ ሴባዮም እስከ ላሳ ይደርሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የከነዓናውያንም ወሰን ከሲዶን አንሥቶ ወደ ጌራራ በኩል ሲል እስከ ጋዛ ስረስ ነው ወደ ሰዶምና ወድደ ገሞራ፥ ወደ አዳማና ወደ ሰቦይም በኩልም ሲል እስከ ላሣድረስ ነው። |
እነዚህ ሁሉ የካም ዘሮች ናቸው፤ እነርሱ በተለያዩ ጐሣዎችና አገሮች ተከፍለው ይኖሩ ነበር፤ እያንዳንዱም ጐሣ የሚነጋገረው በራሱ ቋንቋ ነበር።
እነዚህ አራቱ ነገሥታት፥ ሌሎችን አምስት ነገሥታት ለመውጋት ሄዱ፤ የተዘመተባቸውም አምስት ነገሥታት የሰዶም ንጉሥ ቤራዕ፥ የገሞራ ንጉሥ ቢርሻዕ፥ የአዳማ ንጉሥ ሺንአብ፥ የጸቦይም ንጉሥ ሼሜቤርና ጾዓር ተብላ የምትጠራው የቤላዕ ንጉሥ ነበሩ።
ቀጥሎም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “የሰዶምና የገሞራ ሕዝብ የሚፈጽሙት በደል ምን ያኽል እንደ ሆነ ሰምቼአለሁ፤ ኃጢአታቸውም እጅግ ከባድ መሆን አለበት፤
በአብርሃም ዘመን ከደረሰው ራብ ሌላ ዳግመኛ ራብ በምድር ላይ መጣ፤ በዚህ ምክንያት ይስሐቅ የፍልስጥኤማውያን ንጉሥ አቤሜሌክ ወዳለበት ወደ ገራር ሄደ፤
አሳና ሠራዊቱም እስከ ገራር ድረስ አሳደዱአቸው፤ ከኢትዮጵያ ሠራዊት ብዙ ሰዎች ስላለቁ፥ ሠራዊቱ እንደገና ተንሠራርቶ ሊዋጋ አልቻለም፤ በዚህም ዐይነት ኢትዮጵያውያን በእግዚአብሔርና በሠራዊቱ ድል ሆኑ፤ የይሁዳ ሰዎችም እጅግ የበዛ ምርኮ ወሰዱ፤
የሲዶና ከተማ ሆይ! አንቺ በባሕር አጠገብ የተገነባሽ ጠንካራ ምሽግ ነሽ፤ ነገር ግን አንቺ ባል አግብታ ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወልዳ እንዳላሳደገች ሴት የተዋረድሽ ትሆኚአለሽ።
“እስራኤል ሆይ! እንዴት እተውሃለሁ? እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? በአዳማና በጸቦይም ያደረግኹትንስ፥ እንዴት አደርግብሃለሁ? ለአንተ ያለኝ ፍቅር ታላቅ ስለ ሆነ፥ ይህን ሁሉ ላደርግብህ አልፈቅድም!
ልዑል እግዚአብሔር ለሕዝቡ ርስታቸውን ባከፋፈለ ጊዜ፥ የሰውን ዘር በለያየ ጊዜ፥ እንደ እስራኤል ልጆች ቊጥር ብዛት፥ ለሕዝቡ ድንበርን ሠራላቸው።
አንድ ቀን ሶምሶን የፍልስጥኤማውያን ከተማ ወደሆነችው ወደ ጋዛ ሄደ፤ እዚያም አንዲት አመንዝራ ሴት አይቶ ከእርስዋ ጋር ለማደር ወደ ቤትዋ ገባ፤
በአገሪቱ ላይ በመስፈር በጋዛ ዙሪያ እስካለው ስፍራ ድረስ የምድሪቱን ሰብል ያጠፉ ነበር፤ የበግ፥ የከብትና የአህያ መንጋቸውንም እየነዱ ስለሚወስዱባቸው ለእስራኤላውያን ምንም ነገር አያስቀሩላቸውም ነበር።