ዘፍጥረት 10:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የከነዓን ልጆች በኲሩ ጺዶን፥ ተከታዩ ሔት ይባሉ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከነዓንም፦ የበኵር ልጁ የሲዶን፣ የኬጢያውያን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የከነዓን ልጆች በኲሩ ጺዶን፥ ተከታዩ ሔት ይባሉ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከነዓንም የበኵር ልጁን ሲዶንን፥ ኬጤዎንን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከነዓንም የበኵር ልጁን ሲዶንን፥ |
ይኸውም እኔ በመካከላቸው ከምኖረው ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች መካከል ለልጄ ሚስት እንዳትመርጥ በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ፤
ስለዚህ ማንነትዋን ለማወቅ ዳዊት አንድ መልእክተኛ ልኮ ቤርሳቤህ ተብላ የምትጠራው የኤሊዓም ልጅ፥ የሒታዊው የኦርዮ ሚስት መሆንዋን ተረዳ።
ቀጥለውም ወደ ገለዓድና በሒታውያን ግዛት ውስጥ ወዳለው ወደ ቃዴስ ዘለቁ፤ ከዚያም በኋላ ወደ ዳን፥ ከዳንም ወደ ምዕራብ ታጥፈው ወደ ሲዶና ሄዱ፤
የከነዓን የበኲር ልጅ ጺዶን ሲሆን እንዲሁም ሒታውያን፥ ኢያቡሳውያን፥ አሞራውያን፥ ጌርጌሳውያን፥ ሒዋውያን፥ ዓርቃውያን፥ ሲናውያን፥ አርዋዳውያን፥ ጸማራውያንና ሐማታውያን የከነዓን ልጆች ናቸው።
እነርሱንም ከግብጻውያን እጅ ለማዳን ወርጃለሁ፤ ከግብጽም አውጥቼ አሁን ከነዓናውያን፥ ሒታውያን፥ አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን፥ የሚኖሩባትን፥ በማርና በወተት የበለጸገችውን ሰፊና ለም የሆነችውን ምድር እሰጣቸዋለሁ።
ዛሬ ለእናንተ የምሰጠውን ሕግ ጠብቁ፤ እኔም አሞራውያንን፥ ከነዓናውያንን፥ ሒታውያንን፥ ፈሪዛውያንን፥ ሒዋውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊታችሁ አባርራለሁ፤
የሲዶና ከተማ ሆይ! አንቺ በባሕር አጠገብ የተገነባሽ ጠንካራ ምሽግ ነሽ፤ ነገር ግን አንቺ ባል አግብታ ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወልዳ እንዳላሳደገች ሴት የተዋረድሽ ትሆኚአለሽ።
ፍልስጥኤም የምትጠፋበት ጊዜ ደርሶአል፤ ከሞት ተርፈው ጢሮስንና ሲዶናን የሚረዱት ሁሉ ተቈራርጠው የሚቀሩበት ጊዜ ተቃርቦአል። እኔ እግዚአብሔር፥ ከሞት ተርፈው በባሕር ዳርቻ የምትገኘው የካፍቶር ዘሮች የሆኑትን ፍልስጥኤማውያን በሙሉ እደመስሳለሁ።
እግዚአብሔርም እስራኤላውያን በእነርሱ ላይ ድልን እንዲቀዳጁ አደረጋቸው፤ እስራኤላውያንም መተው በሰሜን እስከ ሚስረፎትማይምና እስከ ታላቂቱ ሲዶና፥ በምሥራቅም እስከ ምጽጳ ሸለቆ ድረስ አሳደዱአቸው፤ ከእነርሱም አንድ ሰው እንኳ ሳይተርፍ ሁሉንም ፈጁአቸው።
ከዚህም በኋላ ዳዊት ሒታዊውን አቤሜሌክንና ከጸሩያ ልጆች የኢዮአብን ወንድም አቢሳን “ከእናንተ ከሁለታችሁ ከእኔ ጋር አብሮ ወደ ሳኦል ሰፈር የሚሄድ ማን ነው?” ሲል ጠየቃቸው። አቢሻይም “እኔ እሄዳለሁ” ሲል መለሰ።