ነገር ግን ይህም ሁሉ ሆኖ ንጉሥ ምናሴ ባደረገው ክፉ ነገር ምክንያት በይሁዳ ላይ የነደደው አስፈሪ የእግዚአብሔር ቊጣ እስከ አሁን ድረስ ገና አልበረደም ነበር።
ዕዝራ 10:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ አለቆቻችን በዚሁ በኢየሩሳሌም ጉዳዩን ያጥኑት፤ ከዚህም በኋላ ባዕድ ሴት ያገባ ሁሉ እያንዳንዱ በሚሰጠው የቀጠሮ ቀን ከሚኖርባት ከተማ መሪዎችና ዳኞች ጋር እየመጣ ውሳኔውን ይቀበል፤ እግዚአብሔር የተቈጣበትም ሁኔታ ሁሉ በዚሁ ዐይነት ይበርዳል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሹሞቻችን በማኅበሩ ሁሉ ምትክ መደረግ ያለበትን ያድርጉ። ከዚያም፣ በዚህ የተነሣ የመጣው የአምላካችን ብርቱ ቍጣ ከእኛ እስኪመለስ ድረስ፣ በየከተሞቻችን ያሉ ባዕዳን ሴቶችን ያገቡ ሁሉ በየከተማው ካሉት ሽማግሌዎችና ዳኞች ጋራ በተወሰነው ቀን ይምጡ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አለቆቻችንም ለጉባኤው ሁሉ ይቁሙ፥ ስለዚህም ነገር የአምላካችን የነደደው ቁጣ ከእኛ እንዲመለስ፥ እያንዳንዳቸው በከተሞቻችን ያሉ እንግዶቹን ሴቶች ያገቡት ሁሉ በተቀጠረው ጊዜ ይምጡ፥ ከእነርሱም ጋር የከተማ ሽማግሌዎችና ፈራጆች ይምጡ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለቆቻችንም በጉባኤው ፋንታ ሁሉ ይቁሙ፤ ስለዚህም ነገር የአምላካችን ጽኑ ቍጣ ከእኛ ይመለስ ዘንድ እንግዶቹን ሴቶች ያገቡት በከተሞቻችን ያሉት ሁሉ በተቀጠረው ጊዜ ይምጡ፤ ከእነርሱም ጋር የከተማው ሁሉ ሽማግሌዎችና ፈራጆች ይምጡ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቆቻችንም በጉባኤው ሁሉ ፋንታ ይቁሙ፤ ስለዚህም ነገር የአምላካችን ጽኑ ቍጣ ከእኛ ይመለስ ዘንድ እንግዶቹን ሴቶች ያገቡት በከተሞቻችን ያሉት ሁሉ በተቀጠረው ጊዜ ይምጡ፤ ከእነርሱም ጋር የከተማ ሁሉ ሽማግሌዎችና ፈራጆች ይምጡ።” |
ነገር ግን ይህም ሁሉ ሆኖ ንጉሥ ምናሴ ባደረገው ክፉ ነገር ምክንያት በይሁዳ ላይ የነደደው አስፈሪ የእግዚአብሔር ቊጣ እስከ አሁን ድረስ ገና አልበረደም ነበር።
አሁንም እነሆ አድምጡኝ! የእግዚአብሔር ቊጣ በእናንተ ላይ ስለ ነደደ እነዚህ እስረኞች ወንድሞቻችሁንና እኅቶቻችሁን ወደየመኖሪያ ስፍራቸው ተመልሰው ይሄዱ ዘንድ ልቀቁአቸው።”
“ከእንግዲህ ወዲህ የእግዚአብሔር ቊጣ ከእኛ እንዲርቅ እነሆ እኔ አሁን ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ለመግባት ወስኛለሁ፤
ለእግዚአብሔር ታዘዙ እንጂ እንደ እነርሱ ልበ ደንዳኖች አትሁኑ፤ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ስጡ፤ ለዘለዓለም ወደ ቀደሰው በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ቤተ መቅደስ ኑ፤ ከእንግዲህ ወዲህ እግዚአብሔር ቊጣውን ከእናንተ እንዲመልስ እርሱን ብቻ አምልኩ፤
ንግግራቸውንም በመቀጠል እንዲህ አሉት፦ “እነሆ እዚህ የተሰበሰበው ሕዝብ ብዙ ነው፤ ከዚህም ጋር በከባድ ሁኔታ እየዘነበ ነው፤ መጠለያ በሌለበት በዚህ ስፍራ መቆም አልቻልንም፤ በዚህ ኃጢአት የተበከልነውም ብዙዎች በመሆናችን ይህን ሁሉ ነገር በአንድ ወይም በሁለት ቀኖች ውስጥ መፈጸም አይቻልም።
ይህም በተነገረ ጊዜ መሹላምና ሻበታይ ተብሎ የሚጠራው አንድ ሌዋዊ ድጋፍ ከሰጡአቸው ከዐሣሔል ልጅ ዮናታንና የቲቅዋ ልጅ ከሆነው ከያሕዘያ በቀር ሌላ ተቃዋሚ አልነበረም።
ሆኖም እግዚአብሔር ለሕዝቡ ምሕረትን አደረገ፤ ኃጢአታቸውን ይቅር አላቸው እንጂ አላጠፋቸውም። ብዙ ጊዜ ቊጣውን መለሰ፤ ብዙ ጊዜም መዓቱን ገታ።
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በእስራኤል ላይ የነደደው ቊጣዬ ይበርድ ዘንድ የእስራኤልን መሪዎች ሁሉ ወስደህ በጠራራ ፀሐይ በሕዝብ ፊት ግደላቸው።”
እግዚአብሔር ከአስፈሪ ቊጣው ተመልሶ ምሕረት ያደርግልህ ዘንድ እንዲወድም ከተወሰነው ሀብት አንዳችም ለራስህ አታስቀር፤ ይህን ብታደርግ ለአባቶችህ በመሐላ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት ቊጥርህን ያበዛዋል።
በእርሱም ላይ እስከ ዛሬ ድረስ የሚታይ ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩበት፤ እግዚአብሔርም ከቊጣው ተመለሰ፤ ስለዚህም ያ ቦታ የአኮር ሸለቆ ተብሎ ይጠራል።