ዘፀአት 2:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ሕፃኑ መልከ መልካም መሆኑን አይታ ሦስት ወር ሸሸገችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ሕፃኑ መልከ መልካም መሆኑን ባየች ጊዜ ሦስት ወር ሸሸገችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴቲቱም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅም ወለደች፤ መልካምም እንደሆነ ባየች ጊዜ ሦስት ወር ሸሸገችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቲቱም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ መልካምም እንደሆነ በአዩ ጊዜ ሦስት ወር ሸሸጉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቲቱም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ መልካምም እንደሆነ ባየች ጊዜ ሦስት ወር ሸሸገችው። |
ዓምራም ዮኬቤድ የተባለችውን የአባቱን እኅት አገባ፤ እርስዋም አሮንንና ሙሴን ወለደችለት። ዓምራም በሕይወት የኖረበት ዘመን 137 ዓመት ነው።
ዓሞራም በግብጽ የተወለደችውን የሌዊን ሴት ልጅ ዮኬቤድን አግብቶ ነበር፤ እርስዋም አሮንና ሙሴ የተባሉትን ሁለት ወንዶች ልጆችንና ማርያም የተባለችውን አንዲት ሴት ልጅ ወለደችለት።
ምድራቸው ምርጥ በሆነ ነገር ሁሉ የተመላ ይሁን፤ በሚቃጠለው ቊጥቋጦ ውስጥ ከተገለጠው አምላክ ጸጋ ይብዛለት። ከወንድሞቹ መካከል ግንባር ቀደም ለሆነው ልዑል ለዮሴፍ ይደረግለት።
ስለዚህም እሴይ ልኮ አስጠራው፤ እርሱ ቀይ፥ መልከ መልካምና ዐይኖቹ የሚያበሩ ጤናማ ወጣት ነበር፤ እግዚአብሔርም ሳሙኤልን “የመረጥኩት ሰው ይህ ነውና ተነሥተህ እርሱን ቀባው!” አለው።