ዘፀአት 18:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም እስራኤልን ለመታደግ እግዚአብሔር በግብጽ ንጉሥና በሕዝቡም ላይ ያደረገውን ድንቅ ነገር ሁሉ ለዐማቱ ተረከለት። እንዲሁም ሕዝቡ በመንገድ ላይ ሳሉ ምን ያኽል ብርቱ ፈተና እንደ ገጠማቸውና እግዚአብሔርም እንዴት እንዳዳናቸው ነገረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም እግዚአብሔር ለእስራኤል ሲል በፈርዖንና በግብጻውያን ላይ ያደረገውን ሁሉ፣ በመንገድም ላይ ስላጋጠማቸው መከራ ሁሉና እግዚአብሔርም እንዴት እንዳዳናቸው ለዐማቱ ነገረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ጌታ በፈርዖንና በግብጽ ላይ ስለ እስራኤል ያደረገውን ሁሉ፥ በመንገድም ያገኛቸውን ድካም ሁሉ፥ ጌታም እንዳዳናቸው ለአማቱ ተረከለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም እግዚአብሔር በፈርዖንና በግብፃውያን ላይ ስለ እስራኤል ያደረገውን ሁሉ፥ በመንገድም ያገኛቸውን ድካም ሁሉ፥ እግዚአብሔርም እንደ አዳናቸው ለአማቱ ነገረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም እግዚአብሔር በፈርዖንና በግብፃውያን ላይ ስለ እስራኤል ያደረገውን ሁሉ፥ በመንገድም ያገኛቸውን ድካም ሁሉ፥ እግዚአብሔርም እንዳዳናቸው ለአማቱ ነገረው። |
“ቃል ኪዳንህንና ዘለዓለማዊ ፍቅርህን የምትጠብቅ፥ ታላቁ፥ ኀያሉና አስፈሪው አምላካችን ሆይ! በእኛ፥ በንጉሦቻችን፥ በመሪዎቻችን፥ በካህኖቻችን፥ በነቢዮቻችን፥ በቅድመ አያቶቻችን፥ እንዲሁም በሕዝብህ ሁሉ ላይ፥ ከአሦር ነገሥታት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፥ የደረሰውን መከራ ሁሉ አስብ።
በመከራ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ ጠራችሁኝ፤ እኔም አዳንኳችሁ፤ ከመሰወሪያ ስፍራዬ፥ ከሞገድ ውስጥ ሰማኋችሁ፤ በክርክር ምንጮች አጠገብ ፈተንኳችሁ።
አምላክ ሆይ፥ ሕዝብህ እስኪያልፍ ድረስ፥ የተቤዠኸው ሕዝብ እስኪያልፍ ድረስ፥ ፍርሀትና ድንጋጤ ወደቀባቸው፤ በሥልጣንህ እንደ ድንጋይ ጸጥ አሉ።
“ምነው በግብጽ ሳለን እግዚአብሔር በገደለን ኖሮ፥ በዚያ ሌላው ቢቀር ሥጋም ሆነ ሌላ ምግብ የፈለግነውን ያኽል መመገብ እንችል ነበረ፤ እናንተ ግን ሁላችንም በራብ እንድናልቅ ወደዚህ በረሓ አወጣችሁን።”
የምድያም ካህን የሆነው የሙሴ ዐማት የትሮ፥ እግዚአብሔር ከግብጽ ምድር መርቶ ባወጣቸው ጊዜ ለሙሴና ለእስራኤል ሕዝብ ያደረገላቸውን ነገር ሁሉ ሰማ፤
መልአኬም ፊት ፊትህ በመሄድ ወደ አሞራውያን፥ ሒታውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ከነዓናውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን ምድር ይወስድሃል፤ እኔም እነርሱን አጠፋቸዋለሁ።
እኔም ይህ ልጄ እኔን ያመልክ ዘንድ እንድትለቀው ነገርኩህ፤ አንተ ግን እምቢ አልክ፤ ስለዚህ አሁን የአንተን የበኲር ልጅ እገድላለሁ።’ ”
እናንተን አይሰማችሁም፤ ከዚያን በኋላ በግብጽ ላይ በታላቅ ፍርድ ብርቱ ቅጣት በማምጣት ሠራዊቴን፥ ሕዝቤን የእስራኤልን ልጆች ከምድረ ግብጽ አስወጣቸዋለሁ።
በዚህ ዐይነት የኀይል ክንዴን በእነርሱ ላይ አንሥቼ እስራኤላውያንን ከአገራቸው በማወጣበት ጊዜ ግብጻውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።”
ሙሴ ለኤዶም ንጉሥ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት መልእክተኞችን ከቃዴስ ላከ፤ “ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ በእኛ ላይ የደረሰውን ችግር ሁሉ ሰምተሃል፤