በኢየሩሳሌም የተሰበሰበውም ሕዝብ ሰባት ቀን ሙሉ የቂጣን በዓል በታላቅ ደስታ አከበረ፤ ሌዋውያኑና ካህናቱም በየቀኑ በዜማ መሣሪያዎቻቸው በመታጀብ እየዘመሩ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤
ዘፀአት 13:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰባት ቀን ሙሉ እርሾ የሌለበት ቂጣ ትበላላችሁ፤ በሰባተኛውም ቀን ለእግዚአብሔር ክብር በዓል ታደርጋላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሰባት ቀን ያለ እርሾ የተጋገረ ቂጣ ትበላላችሁ፤ በሰባተኛውም ቀን ለእግዚአብሔር በዓል ታደርጋላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ ትበላለህ፥ በሰባተኛውም ቀን ለጌታ በዓል ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስድስት ቀን ቂጣ ትበላላችሁ፤ ሰባተኛውም ቀን የእግዚአብሔር በዓል ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ትበላለህ፤ በሰባተኛውም ቀን ለእግዚአብሔር በዓል ይሆናል። |
በኢየሩሳሌም የተሰበሰበውም ሕዝብ ሰባት ቀን ሙሉ የቂጣን በዓል በታላቅ ደስታ አከበረ፤ ሌዋውያኑና ካህናቱም በየቀኑ በዜማ መሣሪያዎቻቸው በመታጀብ እየዘመሩ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤
“ከግብጽ የወጣችሁት በአቢብ ወር ስለ ሆነ የቂጣን በዓል በመጠበቅ በየዓመቱ አክብሩ፤ እንዳዘዝኳችሁ በአቢብ ወር እስከ ሰባት ቀን ቂጣ ብሉ።
እስከ ሰባት ቀን ድረስ የሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ የዕለት ተግባራችሁን ማከናወን ትታችሁ በሰባተኛው ቀን ለአምልኮ ትሰበሰባላችሁ።”
በሚከተሉት ስድስት ቀኖች ደግሞ እርሾ ሳይነካው የተዘጋጀ ቂጣ ትበላለህ፤ በሰባተኛው ቀን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ትሰግድ ዘንድ ጉባኤ ይሁን፤ በዚያ ቀን ሥራ አትሥራበት።