ከእኛ እያንዳንዳችን የሚወለደውን የመጀመሪያ ወንድ ልጅ ወስደን በቤተ መቅደስ ለሚያገለግለው ካህን በማስረከብ፥ ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን እናደርጋለን፤ እንዲሁም ከላሞቻችን፥ ከበጎቻችንና ከፍየሎቻችን የሚወለደውንም ጥጃና ግልገል ሁሉ የመጀመሪያውን ለእግዚአብሔር እንለያለን።
ዘፀአት 13:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኲር የሆነውን ወንድ ልጅ ሁሉ ለእግዚአብሔር ትሰጣላችሁ፤ እንዲሁም የእንስሶቻችሁ በኲር ሁሉ ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእናቱን ማሕፀን የሚከፍተውን ሁሉ ለእግዚአብሔር ትሰጣላችሁ፤ እንደዚሁም እንስሶቻችሁ በመጀመሪያ የወለዷቸው ወንዶች ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማሕፀንን የሚከፍተውን ሁሉ ለጌታ ስጥ፥ የአንተ ከሆነ ከከብት ሁሉ ተባት ሆኖ አስቀድሞ የተወለደው ለጌታ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማሕፀንን የሚከፍተውን ሁሉ ለይ፤ ከመንጋህና ከከብትህም መጀመሪያ የሚወለደው ተባት ለእግዚአብሔር ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማሕፀንን የሚከፍተውን ሁሉ ለእግዚአብሔር ለይ፤ ከሚሆንልህ ከብት ሁሉ ተባት ሆኖ አስቀድሞ የተወለደው ለእግዚአብሔር ይሆናል። |
ከእኛ እያንዳንዳችን የሚወለደውን የመጀመሪያ ወንድ ልጅ ወስደን በቤተ መቅደስ ለሚያገለግለው ካህን በማስረከብ፥ ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን እናደርጋለን፤ እንዲሁም ከላሞቻችን፥ ከበጎቻችንና ከፍየሎቻችን የሚወለደውንም ጥጃና ግልገል ሁሉ የመጀመሪያውን ለእግዚአብሔር እንለያለን።
ከሰበሰብነው መከር የመጀመሪያውን እህል ዱቄት ወስደን በቤተ መቅደስ ለሚያገለግለው ካህን እንሰጣለን፤ ሌላውንም የወይን ጠጅ፥ የወይራ ዘይትና የመሳሰለውንም ፍራ ፍሬ ሁሉ የመጀመሪያውን መባ አድርገን እናቀርባለን። ከእርሻ መንደሮቻችን ግብር ለሚሰበስቡት ሌዋውያንም ምድራችን ከምታበቅለው የእህል መከር ዐሥራት እያወጣን እንሰጣለን።
“ከእስራኤል ሕዝብም ሆነ ከእንስሶቹ በኲር ሆኖ የተወለደ ሁሉ ለእኔ መሆን ይገባዋል፤ ስለዚህ በኲር ሆኖ የተወለደውን ሁሉ ለእኔ እንዲሆን ቀድሰው።”
ነገር ግን የበግ ጠቦት በመተካት የአህያን በኲር ለመዋጀት ትችላላችሁ፤ የማትዋጁት ከሆነ ግን አንገቱን ቈልምሙት፤ በኲር ሆኖ የተወለደውንም ወንድ ልጅ ሁሉ ትዋጃላችሁ። “መባ ሳይዝ ማንም ሰው ባዶ እጁን በፊቴ አይታይ።
የመከር መጀመሪያ የሆነውን ያማረውን በኲራትና ለእኔ የቀረበውን ስጦታ ሁሉ ካህናቱ ይውሰዱ፤ ሕዝቡም ሁልጊዜ እህል ሲፈጩ የዱቄቱን በኲራት ለካህናቱ መባ አድርገው ያበርክቱ፤ እኔም ይህንን ሁሉ የሚያደርጉትን ሕዝብ ቤታቸውን በበረከት እሞላዋለሁ።
“በኲር ሆኖ የሚወለድ እንስሳ ቀድሞውኑ የእግዚአብሔር ስለ ሆነ ማንም ሰው የበጎ ፈቃድ ስጦታ አድርጎ ሊያቀርበው አይችልም፤ እንቦሳም ሆነ የበግና የፍየል ግልገሎች አስቀድመው ለእግዚአብሔር የተለዩ ናቸው፤
“እስራኤላውያን ለእኔ የሚያቀርቡት የሰውም ሆነ የእንስሳ በኲር ሁሉ የእናንተ ይሆናል፤ ነገር ግን የሰውን የበኲር ልጅ ለመዋጀት ዋጋውን በጥሬ ገንዘብ መቀበል አለባችሁ፤ እንዲሁም ንጹሕ ስላልሆነው የእንስሳ በኲር ምትክ ዋጋውን በጥሬ ገንዘብ መቀበል ትችላላችሁ፤
“እነሆ ሌዋውያን የእኔ አገልጋዮች ናቸው፤ የግብጻውያንን በኲር ሁሉ በገደልኩ ጊዜ ከያንዳንዱ እስራኤላዊ የሚወለደውን በኲርና ከእንስሶቹም በኲር የሆነውን ሁሉ ለእኔ የተለየ እንዲሆን አድርጌ ነበር፤ አሁን ግን በኲር ሆነው የሚወለዱትን ወንዶች ልጆች የራሴ በማድረግ ፈንታ ሌዋውያንን መርጬአለሁ፤ እነርሱ የእኔ አገልጋዮች ይሆናሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
በግብጽ ምድር በኲር ሆኖ የተወለደውን በገደልኩ ጊዜ ከእያንዳንዱ እስራኤላዊ ቤተሰብ በኲር ሆኖ የተወለደውንና የእንስሶችንም በኲር ሁሉ ለእኔ የተለየ እንዲሆን ቀድሼው ነበር።
“ከከብትህ ወይም ከበግህ መንጋ የሚወለደውን ወንድ የሆነ በኲር ሁሉ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አድርግ፤ በኲር የሆኑትን በሬዎች ለማንኛውም ተግባር አትጠቀምባቸው፤ እንዲሁም ከበጎች መንጋ በኲሮችን ጠጒራቸውን አትሸልት፤