ዘዳግም 5:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሥራህን ሁሉ በስድስት ቀኖች ሠርተህ ታከናውናለህ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስድስት ቀን ሥራ፤ ተግባርህንም ሁሉ አከናውን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስድስት ቀን ሥራ፥ ሥራህንም ሁሉ አከናውን፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስድስት ቀን ሥራ፤ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስድስት ቀን ሥራ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ፥ |
“በሳምንት ስድስት ቀን ሥራህን ሁሉ ሥራ፤ በሰባተኛው ቀን ግን ምንም ሥራ አትሥራበት፤ በዚህ ዐይነት አገልጋዮችህና ለአንተ የሚሠሩ መጻተኞች፥ እንዲሁም በሬህና አህያህ ዕረፍት አድርገው ይዋሉ።
ሥራ የምትሠሩባቸው ስድስት ቀኖች አሉላችሁ፤ ሰባተኛው ዕለተ ሰንበት ግን የዕረፍት ቀን ነው፤ በዚያን ቀን ለአምልኮ ተሰብሰቡ እንጂ ምንም ሥራ አትሥሩበት፤ በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ሰንበት ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ዕለት ነው፤
ሰባተኛው ቀን ግን ለእኔ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የዕረፍት ቀን ነው፤ በዚያን ቀን ምንም ዐይነት ሥራ አትሥራ፤ አንተም ሆንክ ልጆችህ፥ አገልጋዮችህም ሆኑ እንስሶችህ በአገርህ ውስጥ የሚኖሩ መጻተኞችም ቢሆኑ ምንም ሥራ አትሥሩበት፤ አገልጋዮችህም ልክ እንደ አንተው ዕረፍት ያድርጉ።