ዘዳግም 5:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ ‘የእኔን የእግዚአብሔር አምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ሰው እግዚአብሔር ሳይቀጣው አይቀርም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር አምላክህን ስም በከንቱ አታንሣ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚያነሣውን በደል አልባ አያደርገውምና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ ‘የጌታን የአምላክህ ስም በከንቱ አትጥራ፥ ጌታ ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ሳይቀጣው አይቀርምና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በሐሰት አትጥራ፤ እግዚአብሔር ስሙን በሐሰት የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና። |
ወንድሞቼ ሆይ! ከሁሉም በላይ በሰማይ ወይም በምድር ወይም በሌላ በምንም ነገር አትማሉ፤ ንግግራችሁ አዎ ከሆነ በእውነት አዎ ይሁን፤ አይደለም ከሆነም በእውነት አይደለም ይሁን፤ እንዲህ ካልሆነ ግን ይፈረድባችኋል።