ዘዳግም 4:44 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ ለእስራኤላውያን ያቀረበው ሕግ ይህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ በእስራኤላውያን ፊት የደነገገው ሕግ ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም በእስራኤል ልጆች ፊት ያኖራት ሕግ ይህች ናት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም በእስራኤል ልጆች ፊት ያኖራት ሕግ ይህች ናት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም በእስራኤል ልጆች ፊት ያኖራት ሕግ ይህች ናት፤ |
ለእስራኤላውያን በኢያሪኮ ትይዩ ከዮርዳኖስ ወንዝ ባሻገር ባለው በሞአብ ሜዳ ላይ በነበሩበት ጊዜ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት የሰጣቸው ትእዛዞችና ሥርዓቶች እነዚህ ናቸው።
የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር በማርና በወተት የበለጸገችውን ምድር እንደሚሰጥህ ቃል በገባልህ መሠረት ምድሪቱን ለመያዝ በተሻገርህ ጊዜ የዚህን ሕግ ቃሎች በድንጋዮቹ ላይ ጻፍ፤
ስለዚህም ለሮቤል ነገድ ከፍታ ባለው በረሓ የምትገኘው የቤጼር ከተማ፥ ለጋድ ነገድ በገለዓድ ግዛት የምትገኘው ራሞትና፥ ለምናሴም ነገድ በባሳን ግዛት ውስጥ የምትገኘው ጎላን እንዲለዩ አደረገ።
እስራኤላውያን ከአርኖን ሸለቆ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ በስተምሥራቅ በኩል ወዳለው ወደ አራባ ሁሉ፥ ከዮርዳኖስ ማዶ በስተምሥራቅ በኩል አሸንፈው ምድራቸውን የያዙባቸው ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤