ዘዳግም 33:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቦችን ወደ ተራራ ጠርተው እዚያ ትክክለኛ የሆነውን መሥዋዕት ያቀርባሉ፤ ከባሕር ሀብትን፥ ከአሸዋም ድብቅ የሀብት ክምችትን ያገኛሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሕዛብን ወደ ተራራው ይጠራሉ፤ በዚያም የጽድቅን መሥዋዕት ያቀርባሉ። በባሕሮች ውስጥ ያለውን በተትረፈረፈ ብልጽግና፣ በአሸዋውም ውስጥ የተደበቀውን ሀብት ይደሰቱበታል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተሰወረውን የአሸዋውን መዝገብ፥ የባሕሩንም ባለጠግነት ይጠባሉና አሕዛብን ወደ ተራራው ይጠራሉ፥ በዚያ የጽድቅ መሥዋዕት ይሠዋሉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሕዛብን ያጠፉአቸዋል፤ በዚያም ይጠሩአቸዋል፤ የጽድቅ መሥዋዕትንም ይሠዋሉ፤ የባሕሩም ሀብት፥ በባሕሩ ዳር የሚኖሩ ሰዎችም ገንዘብ ይመግብሃልና፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተሰወረውን የአሸዋውን መዝገብ፥ 2 የባሕሩንም ባለጠግነት ይጠባሉና 2 አሕዛብን ወደ ተራራው ይጠራሉ፤ 2 በዚያ የጽድቅ መሥዋዕት ይሠዋሉ። |
ስለዚህ ብዙ ሕዝቦች እንዲህ ይላሉ፦ “ሕግ ከጽዮን፥ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ስለሚገኝ ኑ ወደ እግዚአብሔር ተራራ እንውጣ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤተ መቅደስም እንሂድ፤ እርሱ ፈቃዱን እንድናደርግ ያስተምረናል፤ እኛም በእርሱ መንገድ እንሄዳለን።”
ልጆች የእናታቸውን ጡት እንደሚጠቡ የአንቺም ልጆች የሕዝቦችንና የነገሥታትን ሀብት በመውሰድ ይጠቀሙበታል፤ አንቺም እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽና ታዳጊሽ ኀያሉ የያዕቆብ አምላክ መሆኔን ታውቂአለሽ።
ይህንንም አይተሽ ፈገግታሽ በደስታ ይፈካል፤ ከባሕር የሚገኘው በረከትና፥ ከሕዝቦች የሚመጣው ሀብት የአንቺ ስለሚሆን፥ ከደስታሽ ብዛት የተነሣ ልብሽ ይፈነድቃል።
ስለዚህ ብዙ ሕዝቦች እንዲህ ይላሉ፥ “ሕግ ከጽዮን፥ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ስለሚገኝ፥ ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ እንውጣ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤተ መቅደስም እንሂድ፤ እርሱ ፈቃዱን እንድናደርግ ያስተምረናል፤ እኛም በእርሱ መንገድ እንሄዳለን።”
“በከፍተኛ ቦታ ላይ አኖረው፤ የምድሩንም ምርት መገበው፤ ከቋጥኝ የተገኘውን ማርና ከድንጋያማ መሬት ከበቀለው ወይራ የተገኘውን ዘይት መገበው።
ወደ ጌታ ኢየሱስ የምትቀርቡትም እንደ ሕያዋን ድንጋዮች መንፈሳዊ ቤት ሆናችሁ ለመታነጽ ነው፤ በዚህ ዐይነት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ቅዱሳን ካህናት ትሆናላችሁ።