ነገር ግን እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ ሲል ገሠጻቸው፤ “በእስራኤላውያን ፊት የተቀደሰ ክብሬን ትገልጡ ዘንድ ስላላመናችሁብኝ፥ ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር የዚህ ሕዝብ መሪዎች ሆናችሁ አትገቡም።”
ዘዳግም 3:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይልቅስ ተነሥና ወደ ፒስጋ ተራራ ላይ ውጣ፤ በዚያም ላይ ሆነህ ዐይንህ የቻለውን ያኽል የአገሪቱን ሰሜንና ደቡብ፥ ምሥራቅና ምዕራብ አሻግረህ ተመልከት፤ ዮርዳኖስን ተሻግረህ መሄድ ከቶ አይፈቀድልህም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ፈስጋ ተራራ ጫፍ ውጣ፤ ወደ ምዕራብና ወደ ሰሜን፣ ወደ ደቡብና ወደ ምሥራቅም ተመልከት። አንተ ዮርዳኖስን ስለማትሻገር፣ ምድሪቱን በዐይንህ ብቻ እያት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን ዮርዳኖስን አትሻገርምና ወደ ፒስጋ ራስ ውጣ፥ ዓይንህንም አንሥተህ ወደ ምዕራብና ሰሜንም ወደ ደቡብም ወደ ምሥራቅም በዓይንህ ተመልከት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህን ዮርዳኖስን አትሻገርምና ወደ ተራራው ራስ ውጣ፤ ዐይንህንም ወደ ባሕር ወደ መስዕም፥ ወደ አዜብም ወደ ምሥራቅም አንሥተህ በዐይንህ ተመልከት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህን ዮርዳኖስን አትሻገርምና ወደ ፈስጋ ራስ ውጣ፤ ዓይንህንም ወደ ምዕራብ ወደ ሰሜንም ወደ ደቡብም ወደ ምሥራቅም አንሥተህ በዓይንህ ተመልከት። |
ነገር ግን እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ ሲል ገሠጻቸው፤ “በእስራኤላውያን ፊት የተቀደሰ ክብሬን ትገልጡ ዘንድ ስላላመናችሁብኝ፥ ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር የዚህ ሕዝብ መሪዎች ሆናችሁ አትገቡም።”
ከዚያም በፒስጋ ተራራ ጫፍ ላይ ወደሚገኘው ወደ ጾፊም መስክ ወሰደው፤ እዚያም ሰባት መሠዊያዎችን ሠርቶ በእያንዳንዱ ላይ አንድ ኰርማና አንድ አውራ በግ ሠዋ።
እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ፥ የእኔ ዕድሜ መቶ ኻያ ዓመት ስለ ሆነ ከእንግዲህ ወዲህ እናንተን መምራት አይቻለኝም፤ ከዚህም በላይ እኔ ዮርዳኖስን እንደማልሻገር እግዚአብሔር ነግሮኛል፤
“በሞአብ ምድር በኢያሪኮ ከተማ ፊት ለፊት ወደሚገኙት የዐባሪም ተራራዎች ሂድ፤ ወደ ነቦ ተራራም ውጣ፤ ከዚያም ለእስራኤል ሕዝብ የማወርሳትን የከነዓንን ምድር አሻግረህ ተመልከት፤