ዘዳግም 3:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ነገር ግን በእናንተው በሕዝቡ ምክንያት እግዚአብሔር ተቈጣኝ፤ ልመናዬንም ማዳመጥ አልፈለገም፤ ይልቁንም በዚህ ፈንታ እንዲህ አለኝ፤ ‘እንግዲህስ በቃህ! ዳግመኛ ይህን ነገር አታንሣ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ግን በእናንተ ሰበብ ተቈጥቶኝ ነበርና አልሰማኝም፤ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “ይበቃል፤ ከእንግዲህ ወዲያ ስለዚህ ነገር አታንሣብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታ ግን በእናንተ ምክንያት ተቆጥቶኝ ነበር፥ አልሰማኝምም፥ ጌታም አለኝ፦ ‘እንግዲህ ይበቃሃል፤ በዚህ ጉዳይ ዳግመኛ አትናገረኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ግን በእናንተ ምክንያት ተቈጣኝ፤ አልሰማኝምም፤ እግዚአብሔርም አለኝ፦ ‘ይበቃሃል፤ በዚህ ነገር ደግመህ አትናገረኝ።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ግን በእናንተ ምክንያት ተቆጣኝ አልሰማኝምም፤ እግዚአብሔርም አለኝ፦ ይበቃሃል፤ በዚህ ነገር ደግመህ አትናገረኝ። |
ኢየሱስ ግን “እናንተ የምትለምኑትን አታውቁም፤ እኔ በቅርብ ጊዜ የምጠጣውን የመከራ ጽዋ መጠጣት ትችላላችሁን?” አላቸው። እነርሱም “አዎ እንችላለን!” አሉ።
ከእነርሱ ጥቂት ራቅ ብሎ ሄደና፥ በመሬት ላይ በግንባሩ ተደፍቶ፥ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “አባት ሆይ! የሚቻል ከሆነ ይህ የመከራ ጽዋ ከእኔ ወዲያ ይለፍ! ነገር ግን የአንተ ፈቃድ ይሁን እንጂ የእኔ ፈቃድ አይሁን።”
እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ፥ የእኔ ዕድሜ መቶ ኻያ ዓመት ስለ ሆነ ከእንግዲህ ወዲህ እናንተን መምራት አይቻለኝም፤ ከዚህም በላይ እኔ ዮርዳኖስን እንደማልሻገር እግዚአብሔር ነግሮኛል፤
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለዘሮቻቸው አወርሳት ዘንድ ለአብርሃም ለይስሐቅና ለያዕቆብ በመሐላ ቃል የገባሁላቸው የተስፋ ምድር ይህች ናት፤ እነሆ፥ እርስዋን በዐይንህ እንድታያት አድርጌአለሁ፤ ወደዚያች መግባት ግን አይፈቀድልህም።”