አምላክህ እግዚአብሔር እንድታደርግ የሚያዝህን ሁሉ አድርግ፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ የምታደርገው ማናቸውም ነገር እንዲከናወንልህ በሙሴ አማካይነት በተሰጠው ሕግ የተጻፉትን የእግዚአብሔርን ሕግና ትእዛዝ፥ ሥርዓትና ፈቃድ ሁሉ ጠብቅ፤
ዘዳግም 29:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድራቸውንም ወርሰን ለሮቤልና ለጋድ ነገዶች እንዲሁም ለእኩሌታ የምናሴ ነገድ ርስት እንዲሆን አከፋፍለን ሰጥተናል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድራቸውንም ወስደን ለሮቤላውያን፣ ለጋዳውያንና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገን ሰጠን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድራቸውንም ወርሰን ለሮቤላውያን፥ ለጋዳውያንና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገን ሰጠን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድራቸውንም ወስደን ለሮቤልና ለጋድ፥ ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገን ሰጠናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድራቸውንም ወስደን ለሮቤልና ለጋድ ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገን ሰጠናቸው። |
አምላክህ እግዚአብሔር እንድታደርግ የሚያዝህን ሁሉ አድርግ፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ የምታደርገው ማናቸውም ነገር እንዲከናወንልህ በሙሴ አማካይነት በተሰጠው ሕግ የተጻፉትን የእግዚአብሔርን ሕግና ትእዛዝ፥ ሥርዓትና ፈቃድ ሁሉ ጠብቅ፤
በእርሱም መሪነት ወደ ከነዓን ምድር እንሻገራለን፤ በዚህ በዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ያለውን የርስት ድርሻችንን ለራሳችን ለማስቀረት ወደ ጦርነት እንሄዳለን።”
ስለዚህ ሙሴ የአሞራውያንን ንጉሥ የሲሖንንና የባሳንን ንጉሥ የዖግን ግዛት በዙሪያቸው ያሉትን ከተሞችና አገሮች ጭምር ለጋድና ለሮቤል ነገዶች እንዲሁም ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠ፤
አንተ ብቻ አይዞህ፤ በርታ፤ አገልጋዬ ሙሴ ለሰጠህም ሕግ ሁሉ እውነተኛ ታዛዥ ሁን፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ ማናቸውም ነገር እንዲሳካልህ ከዚህ ሕግ ከቶ ዝንፍ አትበል፤
ይህን የሕግ መጽሐፍ ምን ጊዜም ከማንበብ አትቈጠብ፤ በእርሱ የተጻፈውን ሁሉ መፈጸም ትችል ዘንድ እርሱን ሌሊትና ቀን አሰላስለው፤ ይህንን ብታደርግ፥ ሁሉ ነገር በተቃና ሁኔታ ይሳካልሃል።