ዘዳግም 29:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እነሆ፥ ዛሬ እናንተ የየነገድ መሪዎቻችሁ፥ ሽማግሌዎቻችሁ፥ ሹሞቻችሁ፥ ሌሎችም የእስራኤል ወንዶች ሁሉና ልጆቻችሁ፥ ሴቶቻችሁ፥ በእናንተ ሰፈር ሆነው እንጨት የሚለቅሙላችሁና ውሃ የሚቀዱላችሁ መጻተኞች፥ ሁላችሁም በእግዚአብሔር አምላካችሁ ፊት ቆማችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ሁላችሁ መሪዎቻችሁና አለቆቻችሁ፣ ሽማግሌዎቻችሁና ሹሞቻችሁ እንዲሁም ሌሎች የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ዛሬ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ቆማችኋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እናንተ ሁላችሁ መሪዎቻችሁና አለቆቻችሁ፥ ሽማግሌዎቻችሁና ሹሞቻችሁ እንዲሁም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ዛሬ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ቆማችኋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁላችሁ፥ የነገዶቻችሁ አለቆች ሽማግሌዎቻችሁም፥ ሹሞቻችሁም፥ ጻፎቻችሁም፥ የእስራኤል ወንድ ሁሉ ዛሬ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ቆማችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁላችሁ፥ አለቆቻችሁም ነገዶቻችሁም ሽማግሌዎቻችሁም ሹማምቶቻችሁም፥ የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ልጆቻችሁም ሴቶቻችሁም በሰፈራችሁም ያለ እንጨትህን የሚቆርጥ ውኃህንም የሚቀዳ መጻተኛ፥ ዛሬ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ቆማችኋል፤ |
የቀሩትም ሰዎች፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎች፥ የቤተ መቅደሱ መዘምራን፥ የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና ለእግዚአብሔር ሕግ ታዛዦች የሆኑ በጐረቤት ከሚኖሩት የባዕዳን አገር ሕዝቦች ራሳቸውን የለዩ፥ ከሚስቶቻቸው፥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆቻቸው ጋር፥
ስለዚህም ካህኑ ዕዝራ ሰባተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን፥ ማስተዋል የሚችል ሕዝብ ሁሉ ሴት፥ ወንድ፥ ልጅ ዐዋቂው በሙሉ ወደተሰበሰቡበት ስፍራ፥ የሕጉን መጽሐፍ አመጣ፤
ስለ ሆነው ነገር ሁሉ እኛ የጽሑፍ ስምምነት ለማድረግ ወሰንን፤ በስምምነቱም ጽሑፍ ላይ መሪዎቻችን፥ ሌዋውያኖቻችንና ካህናቶቻችን ማኅተማቸውን አኖሩበት።
እግዚአብሔር ‘ቃሌን ይሰሙ ዘንድ ስለምፈልግ ሕዝቡን ሰብስብ’ ባለኝ ጊዜ በሲና ተራራ ላይ በእግዚአብሔር ፊት በቆማችሁበት ቀን ‘በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ለእኔ እንዲታዘዙና፥ ልጆቻቸውም እኔን መፍራትን ያውቁ ዘንድ ያስተምሩአቸው’ ያለውን አስታውሱ።
ታናናሾችንና ታላላቆችን ሙታን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ የሕይወት መጽሐፍ የሆነ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ፤ ሙታንም በመጻሕፍቱ ተጽፎ በተገኘው ሥራቸው መሠረት ፍርድ ተቀበሉ፤
እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያንን ለመውጋት ወጡ፤ ስለዚህም እስራኤላውያን አቤንዔዜር ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ሰፈሩ፤ ፍልስጥኤማውያንም አፌቅ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ሰፈሩ፤