የኢየሩሳሌም ሕዝብ ጠላቶች ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን የሕዝቡን ሀብት ዘረፉ፤ ወደ እግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ እንዳይገቡ የተከለከሉ አሕዛብ እንኳ ቤተ መቅደስዋን ሲወሩ ታዩ።
ዘዳግም 23:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የተኰላሸ ወይም የተሰለበ ሰው የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ አባል አይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብልቱ የተቀጠቀጠ ወይም የተቈረጠ ማንኛውም ሰው ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የተኰላሸ ወይም ብልቱም የተሰለበ ሰው ወደ ጌታ ጉባኤ አይግባ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ፍሬ ዘሩ የተቀጠቀጠ፥ አባለ ዘሩም የተቈረጠ ወደ እግዚአብሔር ቤት አይግባ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቍላው የተቀጠቀጠ ብልቱም የተቈረጠ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። |
የኢየሩሳሌም ሕዝብ ጠላቶች ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን የሕዝቡን ሀብት ዘረፉ፤ ወደ እግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ እንዳይገቡ የተከለከሉ አሕዛብ እንኳ ቤተ መቅደስዋን ሲወሩ ታዩ።
“ ‘የአባቱ ሚስቶች ከሆኑት ከየትኛዋም ጋር ግንኙነት በማድረግ የአባቱን ክብር የሚያዋርድ ሁሉ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይበሉ።