ዘዳግም 19:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር የሚኖሩትን ሕዝቦች ደምስሶ ከተሞቻቸውንና ቤቶቻቸውንም ወርሰህ በዚያ መኖር በምትጀምሩበት ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር ምድራቸውን ለአንተ የሚሰጥባቸውን አሕዛብ በሚደመስሳቸው ጊዜና አንተም እነርሱን አስለቅቀህ በከተሞቻቸውና በቤቶቻቸው በምትቀመጥበት ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አምላክህ ጌታ ምድራቸውን ለአንተ የሚሰጥባቸውን አሕዛብ ጌታ እግዚአብሔር በሚደመስሳቸውና አንተም እነርሱን አስለቅቀህ በከተሞቻቸውና በቤቶቻቸው በምትቀመጥበት ጊዜ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አምላክህ እግዚአብሔር ምድራቸውን የሚሰጥህን አሕዛብ ባጠፋቸው ጊዜ፥ በወረስሃቸውም ጊዜ፥ በከተሞቻቸውና በቤቶቻቸውም በተቀመጥህ ጊዜ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር ምድራቸውን የሚሰጥህን አሕዛብ ባጠፋ ጊዜ፥ በወረስሃትም ጊዜ፥ በከተሞቻቸውና በቤቶቻቸውም በተቀመጥህ ጊዜ፥ |
“የቀድሞ አባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ምድር በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ በጥንቃቄ የምትጠብቁአቸው ኅጎችና ሥርዓቶች እነዚህ ናቸው፤
“እግዚአብሔር አምላክህ ለቀድሞ አባቶችህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ በገባላቸው የተሰፋ ቃል መሠረት አንተ ያልገነባሃቸው ታላላቅና የሚያማምሩ ከተሞች ያሉበትን ምድር ይሰጥሃል።
የምትወርሳቸው ቤቶች አንተ ባላኖርከው መልካም ነገር የተሞሉ ይሆናሉ፤ ያልቈፈርካቸውም የውሃ ጒድጓዶች በዚያ ይገኛሉ፤ እንዲሁም አንተ ያልተከልካቸው የወይን ተክሎችና የወይራ ዛፎች ይገኛሉ፤ እግዚአብሔር ወደዚህች ምድር አስገብቶህ በልተህ በምትጠግብበት ጊዜ፥
እናንተ በማረስ ያልደከማችሁበትን የለማ ምድርና ያልሠራችኋቸውንም ከተሞች መኖሪያ አድርጌ ሰጠኋችሁ፤ እነሆ፥ አሁን ያልተከላችሁትን የወይን ተክልና ያልደከማችሁበትን የወይራ ዛፍ ፍሬ እየተመገባችሁ ትኖራላችሁ።’ ”