“በተራቡም ጊዜ ምግብን ከሰማይ ሰጠሃቸው፤ በተጠሙም ጊዜ ውሃን ከአለት አፈለቅህላቸው፤ ለእነርሱ ልትሰጣቸው ቃል የገባህላቸውንም ምድር በቊጥጥራቸው ሥር ያደርጉ ዘንድ አዘዝካቸው።
ዘዳግም 1:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተመልከቱ፤ አገሪቱ ይህችውላችሁ፤ የቀድሞ አባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔርም ባዘዘው መሠረት ገብታችሁ ውረሱአት፤ በመፍራትም ተስፋ አትቊረጡ።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ እግዚአብሔር ምድሪቱን ሰጥቷችኋል፤ አሁንም የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር በነገራችሁ መሠረት ውጡ፤ ውረሷትም፤ አትፍሩ፤ አትደንግጡም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ ጌታ አምላካችሁ ምድሪቱን በፊትህ አኑሮአል፥ የአባቶችህ አምላክ ጌታ እንዳለህ፥ ውጣ፥ ውረሳት፥ አትፍራ፥ አትደንግጥም።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ምድሪቱን በፊታችሁ እንደ ሰጣችሁ እዩ፤ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር እንዳላችሁ ውጡ፤ ውረሷት፤ አትፍሩ፤ አትደንግጡም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ አምላክህ እግዚአብሔር ምድሪቱን በፊትህ አድርጎአል፤ የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር እንዳለህ፥ ውጣ፥ ውረሳት፤ አትፍራ፥ አትደንግጥም አልኋችሁ። |
“በተራቡም ጊዜ ምግብን ከሰማይ ሰጠሃቸው፤ በተጠሙም ጊዜ ውሃን ከአለት አፈለቅህላቸው፤ ለእነርሱ ልትሰጣቸው ቃል የገባህላቸውንም ምድር በቊጥጥራቸው ሥር ያደርጉ ዘንድ አዘዝካቸው።
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ! እኔ አምላክህ ነኝ፥ ተስፋ አትቊረጥ! እኔ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፤ ድል ነሺ በሆነ ክንዴ እደግፍሃለሁ።
ካሌብ ግን በሙሴ ፊት ሕዝቡን ጸጥ በማሰኘት “እነርሱን ድል ለመንሣት የሚያስችል በቂ ኀይል ስለ አለን አገሪቱን አሁኑኑ ሄደን እንያዛት አለ።”
“ጠላቶችህን ለመውጋት ስትዘምት፥ ሠረገሎችንና ፈረሶችን፥ ከአንተ የሚበልጥም ሠራዊት ባየህ ጊዜ ከግብጽ ምድር ያወጣህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ስለ ሆነ አትፍራቸው፤
‘የእስራኤል ሰዎች ሆይ! አድምጡ! እነሆ፥ ዛሬ ወደ ጦርነት መሄዳችሁ ነው፤ ከጠላቶቻችሁ የተነሣ አትፍሩ! ወኔአችሁ አይቀዝቅዝ፤ አትሸበሩም!
ቈራጥነትና ድፍረት ይኑራችሁ፤ ከእነርሱም የተነሣ ከቶ አትፍሩ፤ አትደንግጡም፤ ራሱ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፤ አይጥላችሁም፤ አይተዋችሁም።”
እግዚአብሔር፥ ‘ሂዱ፤ የሰጠኋችሁንም የተስፋ ምድር ውረሱ’ ብሎ ከቃዴስ በርኔ በላካችሁም ጊዜ በእርሱ ላይ ዐመፃችሁ እንጂ አልተማመናችሁበትም፤ ለቃሉም አልታዘዛችሁም።