ዳዊትም “እነሆ እኔ ለምርጫ በሚያስቸግር ሁኔታ ላይ ነኝ! ይሁን እንጂ በሰው እጅ መውደቅ አልፈልግም፤ እግዚአብሔር መሐሪ ስለ ሆነ እርሱ ራሱ ይቅጣኝ!” አለ።
ዳንኤል 9:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታ አምላካችን ሆይ፥ ምንም እኛ በአንተ ላይ ብናምፅ አንተ መሐሪና ይቅር ባይ ነህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምንም እንኳ በርሱ ላይ ያመፅን ብንሆን፣ ጌታ አምላካችን ይቅር ባይና መሓሪ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእርሱ ላይ ምንም እንኳ ያመፅን ብንሆን፥ በባሪያዎቹም በነቢያት እጅ በፊታችን ባኖረው በሕጉ እንሄድ ዘንድ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ቃል ምንም እንኳ ባንሰማ፥ ለጌታ ለአምላካችን ምሕረትና ይቅርታ ነው። |
ዳዊትም “እነሆ እኔ ለምርጫ በሚያስቸግር ሁኔታ ላይ ነኝ! ይሁን እንጂ በሰው እጅ መውደቅ አልፈልግም፤ እግዚአብሔር መሐሪ ስለ ሆነ እርሱ ራሱ ይቅጣኝ!” አለ።
ፊታችንን ወደዚህ ቤተ መቅደስ መልሰን በምንጸልይበት ጊዜ የእኔንና የሕዝብህን ጸሎት ስማ፤ ከመኖሪያህ ከሰማይ ሆነህ ስማን፤ ይቅርም በለን።
ክፉዎች አካሄዳቸውን፥ ኃጢአተኞች ክፉ ሐሳባቸውን ይተዉ፤ ምሕረቱ ብዙ ስለ ሆነ ይቅር ይላቸው ዘንድ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመለሱ።
ለእኛ ስላደረጋቸው ድርጊቶች ሁሉ፥ ለእስራኤል ሕዝብ እንደ መሐሪነቱ ስላሳየው ከፍተኛ በጎ አመለካከት፥ ስለ ተትረፈረፈውም ዘለዓለማዊ ፍቅሩ የእግዚአብሔርን ቸርነት ምስጉን ድርጊቶቹን እዘረዝራለሁ።
ሕዝቤም ወደ እኔ እንዲህ በማለት ይጮኻሉ፤ ‘ምንም እንኳ የበደላችን ብዛት በእኛ ላይ ቢመሰክርም፥ እግዚአብሔር ሆይ! በተስፋ ቃልህ መሠረት እርዳን፤ ከአንተ ርቀናል፤ አንተንም አሳዝነናል።
ነገር ግን እስራኤላውያን በበረሓ ሳሉ እንኳ በእኔ ላይ ዐመፁ፤ ለሚታዘዝለት ሁሉ ሕይወትን የሚያስገኝለትን ሕጌንና ሥርዓቴን ጣሱ፤ ፈጽመውም ሰንበትን አረከሱ፤ በዚያም በበረሓ ቊጣዬን በእነርሱ ላይ በመግለጥ ላጠፋቸው አስቤ ነበር፤
ጌታ ሆይ! አንተ እውነተኛ ነህ፤ ነገር ግን ለአንተ ታማኞች ባለመሆናችን፥ እኛ በምድር ሁሉ ላይ የበተንከን በቅርብና በሩቅ ያለን የይሁዳ ሕዝብ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎችና መላዋ የእስራኤል ሕዝብ በአሁኑ ጊዜ ኀፍረት ደርሶብናል።
እንዲህም ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፦ “እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ይህን እንደምታደርግ ገና በአገሬ ሳለሁ ተናግሬ አልነበረምን? ከፊትህ ኰብልዬ ወደ ተርሴስ ለመሄድ ያቀድኩትም በዚህ ምክንያት ነበር፤ አንተ ቸርና ይቅር ባይ፥ ታጋሽና ምሕረትህ የበዛ፥ በዘለዓለማዊ ፍቅር የተመላህ፥ ቊጣህን መልሰህ ምሕረት የምታደርግ አምላክ መሆንህን ዐውቅ ነበር።