እንዲህም አሉ፦ “ኑ አንድ ከተማ እንመሥርት፤ በዚያም ጫፉ እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ እንዳንበታተን ስማችንን እናስጠራ።”
ዳንኤል 4:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ንጉሥ ሆይ! በበኩሌ የምመክርህን ስማ፤ ኃጢአት መሥራትን ትተህ መልካም ሥራ መሥራትን አዘወትር፤ ክፋትን ትተህ ለተጨቈኑ ሰዎች ራራላቸው፤ ይህን ብታደርግ በሰላም የመኖር ዕድሜህ ይረዝምልህ ይሆናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ንጉሥ ሆይ፤ ምክሬን ስማ፤ ኀጢአት መሥራትን ትተህ ትክክለኛ የሆነውን አድርግ፤ ክፋትን ትተህ ለተጨቈኑት ቸርነትን አድርግ፤ ምናልባት በሰላም የምትኖርበት ዘመን ይራዘምልህ ይሆናል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሥ ሆይ፥ ስለዚህ ምናልባት የደኅንነትህ ዘመን ይረዝም እንደ ሆነ ምክሬ ደስ ያሰኝህ፥ ኃጢአትህንም በጽድቅ፥ በደልህንም ለድሆች በመመመጽወት አስቀር። |
እንዲህም አሉ፦ “ኑ አንድ ከተማ እንመሥርት፤ በዚያም ጫፉ እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ እንዳንበታተን ስማችንን እናስጠራ።”
“አክዓብ በእኔ ፊት ራሱን እንዴት እንዳዋረደ ተመልክተሃልን? ይህን ስላደረገ በሕይወቱ ሳለ መቅሠፍትን አላመጣበትም፤ የተባለውን መቅሠፍት በአክዓብ ቤተሰብ ላይ የማመጣው በልጁ የሕይወት ዘመን ይሆናል።”
የአሦር ንጉሠ ነገሥት በመደንፋት ሲናገር እንዲህ ብሎአል፦ “ይህን ሁሉ ያደረግኹ እኔ ራሴ ነኝ፤ እኔ ብርቱ፥ ዐዋቂና ብልኅ ነኝ፤ በመንግሥታት መካከል የነበረውን ወሰን አፈራረስኩ፤ ያካበቱትንም ሀብት ሁሉ ወሰድኩ፤ በእነዚያም አገሮች የሚኖሩትን ሕዝብ ሁሉ በጀግንነቴ አዋረድኳቸው።
“አንቺ በልብሽ ‘እንደ እኔ ያለ ማንም የለም፤ ባልዋ እንደ ሞተባት ሴት ሆኜ አልኖርም፤ ወይም የልጅ ሞት አይደርስብኝም’ ብለሽ በመዝናናት የተቀመጥሽው ቅምጥሊቱ ሆይ! ይህን ስሚ፦
ተማርካችሁ ሄዳችሁ እንድትኖሩባቸው ላደረግኋቸው ከተሞችም ዕድገት መልካም ነገርን ተመኙ፤ ስለ እነርሱም መልካም ኑሮ ወደ እኔ ጸልዩ፤ እነርሱ መልካም ኑሮ ቢኖሩ እናንተም መልካም ኑሮን ትኖራላችሁ።
እኔም እንዲህ አልኩት፦ “አይዞህ! ለእነርሱ ተላልፈህ አትሰጥም፤ እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል እንድትሰማ እለምንሃለሁ፤ ለአንተም መልካም ነገር ይሆንልሃል፤ ሕይወትህም ከጥፋት ትድናለች።
ልዑል እግዚአብሔር ለግብጽ ንጉሥ እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፤ በወንዝ ውስጥ የተጋደመ አስፈሪ የባሕር አውሬ የምትመስል አንተ! እነሆ፥ እኔ በቊጣ ተነሥቼብሃለሁ፤ ‘የዓባይ ወንዝ የእኔ ነው፤ ይህን ወንዝ የሠራሁት እኔ ነኝ’ ትላለህ።
ግብጽም ባዶዋን ምድረ በዳ ሆና ትቀራለች። በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ። “ ‘አንተ የዓባይ ወንዝ የእኔ ነው፤ ይህን ወንዝ የሠራሁት እኔ ነኝ’ ብለሃልና።
ምናልባት እግዚአብሔር አምላካችሁ ቊጣውን መልሶ፥ በረከቱን ይሰጣችሁ ይሆናል፤ እናንተም በዚያን ጊዜ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር የእህልና የመጠጥ ቊርባን ታቀርባላችሁ።
“ከእኔ በቀር ሌላ የለም” ብላ በመዝናናትና ራስዋን በማስደሰት ትኖር የነበረችው ከተማ እንዴት የአራዊት መመሰጊያ ባድማ ሆነች! በእርስዋ በኩል የሚያልፈው ሁሉ በእጁ እየጠቈመ ያፏጭባታል።
ጳውሎስ ስለ ጽድቅና ራስን ስለ መግዛት ስለሚመጣውም ፍርድ በተናገረ ጊዜ ፊልክስ ፈርቶ “አሁን ሂድ፤ ሲመቸኝ ሌላ ጊዜ አስጠራሃለሁ” አለው።
ነገር ግን አስቀድሜ በደማስቆ ያሉት ሰዎች፥ ቀጥሎም በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ምድር ሁሉ ያሉት እንዲሁም አሕዛብ ጭምር ንስሓ ገብተው ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ አስተማርኳቸው፤ ንስሓ መግባታቸውን የሚያመለክት ነገር እንዲያደርጉም አስተማርኳቸው።
ጌታን መፍራት ምን መሆኑን ስለምናውቅ ሰዎችን እናስረዳለን፤ እኛ ምን መሆናችንንም እግዚአብሔር ያውቃል፤ እናንተም በልቡናችሁ ምን መሆናችንን እንደምታውቁ ተስፋ አደርጋለሁ።
ወንድሞቼ ሆይ! እናንተ ለነጻነት ተጠርታችኋል፤ ነገር ግን አንዱ ሌላውን በፍቅር ያገልግል እንጂ ይህ ነጻነታችሁ የሥጋን ምኞት መፈጸሚያ ምክንያት አይሁን።