በቀድሞ ዘመን እጆችህ ያደረጉትን ድርጊት ሁሉ አባቶቻችን ነግረውናል፤ ይኸውም፥ እነርሱን ለመትከል ሕዝቦችን አባረሃል፤ እነርሱን ለማደላደል ነዋሪዎቹን አጥፍተሃል።
አሞጽ 9:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቤን እስራኤልን በሰጠኋቸው ምድር ላይ እተክላቸዋለሁ፤ ዳግመኛም ከዚያ ተነቅለው አይወጡም፤” ይህን የሚናገር እግዚአብሔር አምላካችሁ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤልን በገዛ ምድራቸው እተክላቸዋለሁ፤ ከሰጠኋቸውም ምድር፣ ዳግመኛ አይነቀሉም፤” ይላል አምላክህ እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድራቸውም ላይ እተክላቸዋለሁ፥ ከእንግዲህም ወዲህ ከሰጠኋቸው ከምድራቸው አይነቀሉም፥” ይላል ጌታ አምላክህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድራቸውም እተክላቸዋለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ከሰጠኋቸው ከምድራቸው አይነቀሉም” ይላል ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር አምላክ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድራቸውም እተክላቸዋለሁ፥ ከእንግዲህም ወዲህ ከሰጠኋቸው ከምድራቸው አይነቀሉም፥ ይላል አምላክህ እግዚአብሔር። |
በቀድሞ ዘመን እጆችህ ያደረጉትን ድርጊት ሁሉ አባቶቻችን ነግረውናል፤ ይኸውም፥ እነርሱን ለመትከል ሕዝቦችን አባረሃል፤ እነርሱን ለማደላደል ነዋሪዎቹን አጥፍተሃል።
በዚህ ፈንታ ‘የእስራኤልን ሕዝብ ከሰሜን አገርና ከሌሎችም እነርሱን ከበተነበት አገር ሁሉ ያስወጣ ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው ይምላሉ፤ ወደገዛ አገራቸውና ለቀድሞ አባቶቻቸው ወደ ሰጠኋቸው ምድር መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
በዚህ ፈንታ፥ የእስራኤልን ሕዝብ ከሰሜን ምድርና ተበታትነው ከነበሩባቸው ሌሎች አገሮች ሰብስቤ ባመጣኋቸው በእኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም ይምላሉ፤ ከዚያም በኋላ በገዛ ምድራቸው ይኖራሉ።”
እስራኤልና ይሁዳ አንድ ይሆናሉ፤ ሁለቱም በአንድነት በስተሰሜን ካለው አገር ከምርኮ ይመለሳሉ፤ ለቀድሞ አባቶቻችሁ የዘለዓለም ርስት አድርጌ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ተመልሰው ይገባሉ።”
እንደ እሳት በሚነደው ታላቅ ቊጣዬ የበተንኳቸውን ሕዝብ ከተበተኑባቸው አገሮች ሁሉ እንደገና ወደዚህ ቦታ እሰበስባቸዋለሁ፤ በሰላም እንዲኖሩም አደርጋለሁ።
እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕዝቤን ሁሉ ከተበተኑባቸው ሕዝቦች መካከል በአንድነት ሰብስቤ ወደገዛ ምድራቸው መልሼ የማመጣቸው መሆኔን ንገራቸው።
ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠሁትና የቀድሞ አባቶቻቸውም በኖሩባት ምድር ይኖራሉ፤ በዚያችም ምድር እነርሱና ልጆቻቸው ዘሮቻቸውም ሳይቀሩ ለዘለዓለም ይኖራሉ፤ እንደ አገልጋዬ እንደ ዳዊት ያለ ንጉሥ በእነርሱ ላይ ለዘለዓለም ይነግሣል።
ስለዚህ እስከ አሁን ድረስ ሳልበቀልላቸው የቀረሁትን የንጹሐንን ደም እበቀላለሁ፤ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ግን ለዘለዓለም ለሕዝቤ መኖሪያ ይሆናሉ፤ እኔም እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ ላይ እኖራለሁ።”
እያንዳንዱ ሰው በተከለው ወይንና በለስ ጥላ ሥር በሰላም ያርፋል። የሚያስፈራውም ነገር አይኖርም፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።