አሞጽ 2:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በሞአብ ምድር እሳት እለቅበታለሁ፤ የቂሪዮትንም ምሽጎች ያቃጥላል፤ ጦረኞች ድንፋታ፥ ጩኸትና የመለከት ድምፅ እያሰሙ የሞአብን ሕዝብ ይጨርሳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቂርዮትን ምሽጎች እንዲበላ፣ በሞዓብ ላይ እሳት እሰድዳለሁ፤ ሞዓብ በጦርነት ጩኸትና በመለከት ድምፅ መኻል፣ በታላቅ ሁካታ ውስጥ ይሞታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሞዓብ ላይ እሳትን እልካለሁ፥ የቂርዮትንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች፤ ሞዓብም በውካታና በጩኸት በመለከትም ድምፅ መካከል ይሞታል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሞዓብ ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፤ የከተሞችዋንም መሠረቶች ትበላለች፤ ሞዓብም በድካምና በውካታ፥ በመለከትም ድምፅ ይሞታል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሞዓብ ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፥ የቂርዮትንም አዳራሾች ትበላለች፥ ሞዓብም በውካታና በጩኸት በመለከትም ድምፅ ይሞታል፥ |
“የሐሴቦንና የዔልዓሌ ሕዝብ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይጮኻሉ፤ ጩኸታቸውም እስከ ያሀጽ ተሰምቶአል፤ ከጾዓር እስከ ሖሮናይምና ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ተሰምቶአል፤ የኒምሪም ውሃ እንኳ ደርቆአል።
በሽሽት የደከሙ ስደተኞች በሐሴቦን ጥላ ሥር ተጠልለዋል፤ ይህም የሆነው እሳት ከሐሴቦን፥ ነበልባልም ከሲሆን ቤቶች ወጥቶ የሞአብን ግንባር ቀደም ሠራዊትና ደጋፊ መሪዎችዋን አቃጥሎአል።
ስለዚህ በራባ ከተማ ቅጽር ላይ እሳት እለቅበታለሁ፤ ምሽጎችዋንም ያቃጥላል፤ ከዚህ በኋላ በጦርነቱ ቀን ጩኸትና ሁካታ ይበዛል፤ ጦርነቱም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይፈጥናል፤