አሞጽ 2:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ቀን እጅግ ብርቱ የሆኑ ጦረኞች እንኳ የጦር መሣሪያቸውን እየጣሉ ይሸሻሉ፤” እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጐበዞቹ ተዋጊዎች እንኳ፣ በዚያ ቀን ዕራቍታቸውን ይሸሻሉ፤” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ ቀን በኃያላኑም መካከል ልበ ሙሉው ዕራቁቱን ሆኖ ይሸሻል፥” ይላል ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልበ ሙሉው ኀይለኛም በኀይሉ አይተማመንም፤ ነገር ግን በዚያ ቀን ዕራቁቱን ሆኖ ይሸሻል” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኃያላኑም መካከል ልበ ሙሉው በዚያ ቀን ዕራቁቱን ሆኖ ይሸሻል፥ ይላል እግዚአብሔር። |
የሐጾር ንጉሥ ያቢን ከሔቤር ቤተሰብ ጋር ሰላም መሥርቶ ይኖር ስለ ነበር ሲሣራ ሸሽቶ የቄናዊው የሔቤር ሚስት ወደሆነችው ወደ ያዔል ድንኳን ገባ።