ሐዋርያት ሥራ 6:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ በሸንጎው የተገኙት ሁሉ እስጢፋኖስን ትኲር ብለው ሲመለከቱት ፊቱ እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ታያቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሸንጎው ተቀምጠው የነበሩትም ሁሉ እስጢፋኖስን ትኵር ብለው ሲመለከቱት ፊቱ የመልአክ ፊት መስሎ ታያቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሸንጎም የተቀመጡት ሁሉ ትኩር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሸንጎም ተቀምጠው የነበሩት ሁሉ ትኩር ብለው ተመለከቱት፤ ፊቱንም እንደ እግዚአብሔር መልአክ ፊት ሆኖ አዩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሸንጎም የተቀመጡት ሁሉ ትኵር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት። |
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በወንድሙ ላይ የሚቈጣ ሁሉ ይፈረድበታል፤ ደግሞም ወንድሙን፥ ‘አንተ የማትረባ!’ ብሎ የሚሳደብ በሸንጎ ይፈረድበታል፤ ‘ደደብ!’ ብሎ የሚሳደብ ሁሉ በገሃነመ እሳት ይፈረድበታል።
እኛ ሁላችን ባልተሸፈነ ፊት ሆነን በመስታዋት እንደሚታይ ዐይነት የጌታን ክብር እናንጸባርቃለን፤ እኛም መንፈስ የሆነውን የጌታን መልክ ለመምሰል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።