ሐዋርያት ሥራ 2:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ በጳርቴ፥ በሜድ፥ በዔላም፥ በመስጴጦምያ፥ በይሁዳ፥ በቀጰዶቅያ፥ በጳንጦስ፥ በእስያ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛ የጳርቴና፣ የሜድ፣ የኢላሜጤም ሰዎች፣ በመስጴጦምያ፣ በይሁዳ፣ በቀጰዶቅያ፣ በጳንጦስ፣ በእስያ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጳርቴና የሜድ የኢላሜጤም ሰዎች፥ በመስጴጦምያም በይሁዳም በቀጰዶቅያም በጳንጦስም በእስያም፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛ በተወለድንበት በጳርቴ፥ በሜድ፥ በኢላሜጤ፥ በሁለቱ ወንዞች መካከል፥ በይሁዳ፥ በቀጰዶቅያ፥ በጳንጦስና በእስያ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጳርቴና የሜድ የኢላሜጤም ሰዎች፥ በሁለት ወንዝም መካከል በይሁዳም በቀጰዶቅያም በጳንጦስም በእስያም፥ |
የአብርሃም ንብረት ኀላፊ የነበረው መጋቢ ከጌታው ቤት ምርጥ የሆኑ የስጦታ ዕቃዎችን በዐሥር ግመሎች ጭኖ በሰሜን መስጴጦምያ ናኮር ወደሚኖርበት ከተማ ሄደ።
ይኸውም ሆሴዕ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት ሰልምናሶር ድል አድርጎ ሰማርያን ያዘ፤ እስራኤላውያንንም ማርኮ በእስረኛነት ወደ አሦር ወሰዳቸው፤ ከእነርሱም ጥቂቶቹ በሐላሕ ከተማ፥ ጥቂቶቹ በጎዛን አውራጃ ውስጥ በሚገኘው በሐቦር ወንዝ አጠገብ፥ እንዲሁም ሌሎቹ በሜዶን ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ።
ዐሞናውያን በገዛ እጃቸው ዳዊትን ጠላት እንዳደረጉት ተገነዘቡ፤ ስለዚህም ሠላሳ አራት ሺህ ኪሎ የሚመዝን ብር ከፍለው ሠረገሎችንና ፈረሰኞችን ከላይኛው መስጴጦምያና የሶርያ ግዛቶች ከሆኑት ከማዕካና ከጾባ ተከራዩ፤
ነገር ግን በባቢሎን ከተማ ሳይሆን በሜዶን ክፍለ ሀገር በተለይ “አሕምታ” ተብላ በምትጠራው ከተማ ውስጥ አንድ የብራና ጥቅል ተገኘ፤ በውስጡም የተጻፈበት ቃል እንዲህ የሚል ነበር፦
በዚያን ጊዜ ጌታ እንደገና የኀይል ሥራ ይሠራል፤ ይኸውም በአሦር፥ በግብጽ፥ በጳጥሮስ አገሮች፥ በኢትዮጵያ፥ በዔላም፥ በባቢሎንና በሐማት እንዲሁም በባሕር ጠረፍ አገሮችና በደሴቶች ሁሉ የሚኖሩትን የቀሩት ወገኖቹን ወደ አገራቸው ይመልሳቸዋል።
አስፈሪ የሆነ ራእይ ተገልጦልኛል፤ ይኸውም አንዱ ሌላውን አሳልፎ ይሰጣል፤ ከዳተኛው ይከዳል፤ ዘራፊውም ይዘርፋል። የዔላም ሠራዊት ሆይ! አደጋ ለመጣል ውጡ! የሜዶን ሠራዊት ሆይ! ከተሞችን ክበቡ! እግዚአብሔር በባቢሎን ምክንያት የደረሰውን ሥቃይ ሁሉ ያስወግዳል።
እዚያ የጳንጦስ ተወላጅ የሆነውን አቂላ የሚባል አንድ አይሁዳዊ ሰው አገኘ፤ የሮም ንጉሠ ነገሥት ቀላውዴዎስ አይሁድ ሁሉ ከሮም እንዲወጡ አዞ ስለ ነበረ አቂላ ከሚስቱ ከጵርስቅላ ጋር ከኢጣልያ ገና መምጣቱ ነበር፤ ስለዚህ ጳውሎስ ወደ እነርሱ ሄዶ ተዋወቃቸው፤
በዚህ ዐይነት ይህ የእኛ ሥራ መናቁ ነው፤ ይህም ብቻ ሳይሆን በእስያና በመላው ዓለም ሰው ሁሉ የሚያመልካት የታላቂቱ አምላክ የአርጤሚስ ቤተ መቅደስ ከንቱ ሆኖ መቅረቱ ነው፤ የእርስዋም ታላቅነት መሻሩ ነው።”
ከእስያ አገር ባለሥልጣኖችም ወዳጆቹ የሆኑ አንዳንዶቹ ወደ ጳውሎስ ሰው ልከው “ወደ ሕዝብ መሰብሰቢያው ቦታ ሄደህ እንዳትታይ” ሲሉ ለመኑት።
ጳውሎስ በእስያ ጊዜ እንዳያባክን ብሎ ኤፌሶንን አልፎ ለመሄድ ፈለገ፤ ይህንንም ያደረገው ለጰንጠቆስጤ በዓል በኢየሩሳሌም ለመገኘት አስቦ ስለ ነበር ነው።
ወደ እርሱ በመጡም ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “ወደ እስያ ከገባሁበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ከእናንተ ጋር እንዴት እንደ ኖርኩ እናንተ ታውቃላችሁ፤
የጲርሁስ ልጅ ሶጳጥሮስ ከቤርያ፥ አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ ከተሰሎንቄ፥ ጋይዮስ ከደርቤ፥ ጢሞቴዎስ፥ ቲኪቆስና ጥሮፊሞስ ከእስያ አብረውት ሄዱ።
በቤተ መቅደስም ያገኙኝ ይህንኑ ሳደርግ ነው፤ በዚያን ጊዜ የመንጻትን ሥርዓት ፈጽሜ ነበር፤ ከእኔ ጋር ብዙ ሕዝብ አልነበረም፤ ሁከትም አልተነሣም።
በእስያ የባሕር ዳርቻ ወዳሉት ወደቦች በሚሄደው የአድራሚጥዮን መርከብ ተሳፍረን ተጓዝን፤ በተሰሎንቄ የሚኖረው የመቄዶንያው ሰው አርስጥሮኮስም ከእኛ ጋር ነበረ።
በዚያን ጊዜ “የነጻ ወጪዎች ምኵራብ” ከተባለው የአይሁድ ጸሎት ቤት ሰዎች፥ ከቀሬናና ከእስክንድርያ ሰዎች፥ ከኪልቅያና ከእስያ አንዳንድ ሰዎች ተነሥተው እስጢፋኖስን በመቃወም ይከራከሩት ነበር።
እስጢፋኖስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ወንድሞቼና አባቶቼ ሆይ! እስቲ ስሙኝ! አባታችን አብርሃም በካራን ለመኖር ከመሄዱ በፊት ገና በመስጴጦምያ ሳለ የክብር አምላክ ተገለጠለትና
በእነርሱ ቤት ለጸሎት ለሚሰበሰቡት ምእመናንም ሰላምታ አቅርቡልኝ። በእስያ ክፍለ ሀገር በመጀመሪያ በክርስቶስ ላመነውና ለምወደው ለኤጴኔጦስ ሰላምታ አቅርቡልኝ።
በእስያ ያሉ አብያተ ክርስቲያን ሰላምታ ያቀርቡላችኋል፤ አቂላና ጵርስቅላ፥ በቤታቸው የሚሰበሰቡ ክርስቲያኖችም ሁሉ ልባዊ ሰላምታ በጌታ ስም ያቀርቡላችኋል።
ወንድሞች ሆይ! በእስያ ክፍለ ሀገር በነበርንበት ጊዜ የደረሰብንን መከራ እንድታውቁ እንወዳለን፤ ይህም የደረሰብን መከራ ልንሸከመው ከምንችለው በላይ ወድቆብን ስለ ነበር በሕይወት ለመኖር የነበረን ተስፋ እንኳ ተቋርጦ ነበር።
እናንተ ከግብጽ ምድር ወጥታችሁ በጒዞ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ እነርሱ እህልና ውሃ አንሰጥም ብለው ከልክለዋችሁ እንደ ነበር አይዘነጋም፤ ከዚሁም ጋር በመስጴጦምያ ፐቶር ተብላ በምትጠራው ከተማ ይኖር የነበረ የቢዖር ልጅ በለዓም እንዲረግማችሁ ቀጥረውት ነበር።
የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነው ከጴጥሮስ፥ መጻተኞች ሆናችሁ በጳንጦስ፥ በገላትያ፥ በቀጰዶቅያ፥ በእስያ፥ በቢታንያ ተበታትናችሁ ለምትኖሩት
“የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያን፥ ማለትም ወደ ኤፌሶን፥ ወደ ሰምርኔስ፥ ወደ ጴርጋሞን፥ ወደ ትያጥሮን፥ ወደ ሰርዴስ፥ ወደ ፊላደልፍያና ወደ ሎዶቅያ ላክ።”
ከዮሐንስ ለሰባቱ የእስያ አብያተ ክርስቲያን። ካለው፥ ከነበረውና፥ ከሚመጣው ከእግዚአብሔር፥ በዙፋኑ ፊት ካሉት ከሰባቱ መንፈሶች፥ እንዲሁም ከሞት በመነሣት በኲር ከሆነው የምድር ነገሥታት ገዢ፥ ታማኝ ምስክር ከሆነው፥ ከሚወደንና በደሙ ከኃጢአታችን ነጻ ካወጣን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
ከዚህም የተነሣ የእግዚአብሔር ቊጣ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ነደደ፤ ለመስጴጦምያው ንጉሥ ለኩሻን ፊሽዓታይም አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ለኩሻን ሪሽዓታይም ስምንት ዓመት ተገዙለት፤