ሐዋርያት ሥራ 15:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልባቸውን በእምነት ስላነጻ በእኛና በእነርሱ መካከል ምንም ልዩነት አላደረገም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልባቸውንም በእምነት በማንጻት፣ በእኛና በእነርሱ መካከል ምንም ልዩነት አላደረገም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልባቸውንም በእምነት ሲያነጻ በእኛና በእነርሱ መካከል አንዳች አልለየም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልባቸውንም በእምነት አንጽቶ ከእኛ አልለያቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልባቸውንም በእምነት ሲያነጻ በእኛና በእነርሱ መካከል አንዳች አልለየም። |
ዘላቂ ርስትም ትሁንላችሁ፤ ልጆች ወልደው በመካከላችሁ የሚኖሩ ባዕዳንም ምድሪቱን በምትካፈሉበት ጊዜ የራሳቸው ድርሻ ይኑራቸው፤ እንደማንኛውም እስራኤላውያን ዜጋ ተቈጥረው ምድሪቱን ከሚካፈሉት ከእስራኤል ነገዶች ጋር ዕጣ እንዲጣልላቸው ያስፈልጋል።
እንዲህም አላቸው፦ “አይሁዳዊ ለሆነ ሰው ከሌላ ሕዝብ ጋር ለመተባበርና ወደ ቤቱም ለመግባት በሃይማኖታችን ሕግ እንደማይፈቀድ እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ፤ ነገር ግን ማንንም ንጹሕ ያልሆነ ወይም ርኩስ እንዳልል እግዚአብሔር ገልጦልኛል።
ያላንዳች ማመንታት ከእነርሱ ጋር እንድሄድም መንፈስ ቅዱስ ነገረኝ፤ እነዚህ ስድስት ወንድሞችም ከእኔ ጋር ነበሩ፤ ከእነርሱም ጋር አብረን ቆርኔሌዎስ ወደ ተባለው ሰው ቤት ገባን።
በኢቆንዮን ጳውሎስና በርናባስ አብረው ወደ አይሁድ ምኲራብ ገቡ፤ በዚያም ብዙ አይሁድና ከአሕዛብ እጅግ ብዙ ሰዎች እስኪያምኑ ድረስ አስተማሩ።
እዚያም በደረሱ ጊዜ አማኞችን በአንድነት ሰብስበው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ሆኖ ያደረገውን ሁሉና አሕዛብም እንዲያምኑ እንዴት አድርጎ በር እንደ ከፈተላቸው ነገሩአቸው።
ታዲያ፥ እኛ አይሁድ ከአሕዛብ እንበልጣለን ማለት ነውን? ከቶ አይደለም! ሰዎች ሁሉ አይሁድም ሆኑ አሕዛብ ኃጢአተኞች መሆናቸውን ቀደም ብዬ አስረድቻለሁ።
በቆሮንቶስ ከተማ ለምትገኘው የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ በውስጥዋም በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱትና ቅዱሳን እንዲሆኑ ለተጠሩት፥ እንደዚሁም በየቦታው ለእነርሱና ለእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ለሚጠሩት ሁሉ።
ይህም የሚያመለክተው አሕዛብ ከአይሁድ ጋር የርስቱ ወራሾችና የአንድ አካል ክፍሎች ሆነው እግዚአብሔር ለሰጠው ተስፋ በወንጌል አማካይነት በኢየሱስ ክርስቶስ ተካፋዮች መሆናቸውን ነው።
በዚህ ሁኔታ በግሪካዊና በአይሁዳዊ፥ በተገረዘና ባልተገረዘ፥ በሠለጠነ አረመኔና ባልሠለጠነ አረመኔ፥ ነጻነት በሌለውና ነጻነት ባለው ሰው መካከል ልዩነት የለም፤ ክርስቶስ ሁሉም ነው፤ በሁሉም ነው።
ለምእመናን ቅንነት የተሞላበት ፍቅር እንዲኖራችሁ ለእውነት በመታዘዝ ነፍሳችሁን አንጽታችኋል፤ ስለዚህ በሙሉ ልባችሁ እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።