ከዚህ በኋላ ኤልያቄምና ሼብና እንዲሁም ዮአሕ በሐዘን ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ቀርበው የአሦራውያን ባለሥልጣን የተናገረውን አስረዱት።
ሐዋርያት ሥራ 14:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሐዋርያቱ ጳውሎስና በርናባስ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ በሐዘን ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ወደ ሕዝቡ ሮጡና እየጮኹ እንዲህ አሉ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐዋርያቱ በርናባስና ጳውሎስ ይህን በሰሙ ጊዜ ልብሳቸውን ቀድደው ወደ ሕዝቡ መካከል ሮጡ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው እንዲህ አሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐዋርያት በርናባስና ጳውሎስ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ልብሳቸውን ቀደው ወደ ሕዝቡ መካከል እየጮኹ ሮጡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐዋርያት በርናባስና ጳውሎስም በሰሙ ጊዜ፥ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ፈጥነውም እየጮኹ ወደ ሕዝቡ ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሐዋርያት በርናባስና ጳውሎስ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ልብሳቸውን ቀደው ወደ ሕዝቡ መካከል እየጮኹ ሮጡ፥ |
ከዚህ በኋላ ኤልያቄምና ሼብና እንዲሁም ዮአሕ በሐዘን ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ቀርበው የአሦራውያን ባለሥልጣን የተናገረውን አስረዱት።
የእስራኤልም ንጉሥ ደብዳቤውን ባነበበ ጊዜ በቊጣ ልብሱን ቀደደ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ “የሶርያ ንጉሥ ይህን ሰው እንደምፈውስለት አድርጎ እንዴት ይገምታል? እኔ ሰውን ከቈዳ በሽታ እፈውስ ዘንድ የማዳንና የመግደል ሥልጣን ያለኝ እግዚአብሔር መሰልኩትን? በእርግጥ ይህ አባባል ከእኔ ጋር ጠብ መፈለጉን በግልጥ ያሳያል!” አለ።
በዚህ ጊዜ የካህናት አለቃው በብስጭት ልብሱን ቀደደና እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ተናግሮአል! እናንተም ስድቡን ሰምታችኋል! ከዚህ የበለጠ ምን ምስክር ያስፈልጋል!
እኔ ነጻነት ያለኝ ሰው አይደለሁምን? እኔ ሐዋርያ አይደለሁምን? እኔ ጌታችንን ኢየሱስን አላየሁትምን? እናንተስ በጌታ የሥራዬ ውጤት አይደላችሁምን?