2 ጢሞቴዎስ 1:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ምክንያት እጆቼን በአንተ ላይ በጫንኩ ጊዜ የተሰጠህንና እንደ እሳት ሆኖ በአንተ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ስጦታ እንደገና እንድታቀጣጥለው አሳስብሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በእጆቼ መጫን የተቀበልኸውን በአንተ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ስጦታ እንድታቀጣጥል አሳስብሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህም ምክንያት እጆቼን ስጭን የተሰጠህን በአንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ስጦታ እንድታቀጣጥል አሳስብሃለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ምክንያት እሳት እንደሚያቀጣጥል ሰው እጆቼን በመጫኔ በአንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ስጦታ እንድታነሣሣ አሳስብሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ምክንያት፥ እሳት እንደሚያቀጣጥል ሰው፥ እጆቼን በመጫኔ በአንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ስጦታ እንድታነሣሣ አሳስብሃለሁ። |
ሙሴም ባጽልኤልንና ኦሆሊአብን፥ እንዲሁም እግዚአብሔር ልዩ ችሎታ የሰጣቸውንና ለመርዳት ፈቃደኞች የነበሩትን ሌሎችን ጥበበኞች ሁሉ ጠርቶ ሥራውን እንዲጀምሩ ነገራቸው።
እርሱ ከመሄዱ በፊት ከአገልጋዮቹ ዐሥሩን ጠርቶ ለእያንዳንዱ ዐሥር ምናን ሰጣቸውና ‘ተመልሼ እስክመጣ ድረስ በዚህ ገንዘብ ነግዱ’ አላቸው።
ይህን ትምህርት ለአማኞች ብታስገነዝብ የእምነትን ቃልና የምትከተለውን መልካም ትምህርት እየተመገብክ ያደግኽ፥ የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም አገልጋይ ትሆናለህ።
ይህን ነገር አስገንዝባቸው፤ በቃላት ምክንያት እንዳይከራከሩም በጌታ ፊት አስጠንቅቃቸው፤ ይህ የቃላት ክርክር የሚሰሙትን ሰዎች ያጠፋል እንጂ ለምንም አይጠቅምም።
ወዳጆች ሆይ! ይህ የምጽፍላችሁ ሁለተኛው መልእክት ነው፤ ሁለቱንም መልእክቶች የጻፍኩላችሁ እነዚህን ነገሮች በማስታወስ ቅን አስተሳሰብ እንዲኖራችሁ ላነቃቃችሁ ብዬ ነው።
ይህን ሁሉ አስቀድማችሁ አንድ ጊዜ የምታውቁት ቢሆንም እንኳ ጌታ ሕዝቡን ከግብጽ አገር አውጥቶ እንዳዳነና ያላመኑትንም በኋላ እንዳጠፋቸው ላስታውሳችሁ እወዳለሁ።