Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ጢሞቴዎስ 4:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ትንቢት በተነገረልህ ጊዜና የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችም እጃቸውን በጫኑብህ ጊዜ የተሰጠህን በአንተ ያለውን መንፈሳዊ ስጦታ አትዘንጋ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ሽማግሌዎች እጃቸውን በአንተ ላይ ሲጭኑ በትንቢት የተሰጠህን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ሽማግሌዎች እጃቸውን በአንተ ላይ የጫኑ ጊዜ በትንቢት የተሰጠህን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በትንቢት ከሽማግሌዎች እጅ መጫን ጋር የተሰጠህን በአንተ ያለውን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በትንቢት ከሽማግሌዎች እጅ መጫን ጋር የተሰጠህን፥ በአንተ ያለውን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል።

Ver Capítulo Copiar




1 ጢሞቴዎስ 4:14
18 Referencias Cruzadas  

በዚህ ምክንያት እጆቼን በአንተ ላይ በጫንኩ ጊዜ የተሰጠህንና እንደ እሳት ሆኖ በአንተ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ስጦታ እንደገና እንድታቀጣጥለው አሳስብሃለሁ።


ልጄ ጢሞቴዎስ ሆይ! ከዚህ ቀደም ስለ አንተ በትንቢት በተነገረው መሠረት የሚከተለውን ትእዛዝ በዐደራ እሰጥሃለሁ፤ ትንቢቱን በመከተል መልካም ጦርነትን ተዋጋ፤


እነዚህን በሐዋርያት ፊት አቆሙአቸው፤ ሐዋርያትም ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው።


እጆችህን በመጫን ማንንም ለመሾም አትቸኲል፤ ራስህን በንጽሕና ጠብቅ እንጂ ከሌሎች ሰዎች ጋር በኃጢአት አትተባበር።


የመንፈስ ቅዱስን ሥራ አታዳፍኑ፤


እነርሱም ጾመውና ጸልየው እጆቻቸውን ከጫኑባቸው በኋላ ላኳቸው።


ስለዚህ ጴጥሮስና ዮሐንስ፥ እጆቻቸውን በጫኑባቸው ጊዜ ሰዎቹ መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ።


ጳውሎስ እጁን በጫነባቸውም ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ ወረደና በሌላ ቋንቋዎች ተናገሩ፤ ትንቢትንም መናገር ጀመሩ።


መዋጮም አድርገው በበርናባስና በሳውል እጅ ለቤተ ክርስቲያን መሪዎች ላኩ።


ይህም እውነት መሆኑን የካህናት አለቃውና የሽማግሌዎች ሸንጎ በሙሉ ይመሰክሩልኛል። እንዲያውም በደማስቆ ያሉትን እነዚህን ሰዎች አስሬ ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣትና ለማስቀጣት የሚያስችለኝን በደማስቆ ወደሚገኙት ወገኖቻቸው የጻፉትን ደብዳቤ የተቀበልኩት ከእነርሱ ነው።


መሻሻልህን ሰዎች ሁሉ እንዲያዩ በእነዚህ ነገሮች ትጋ፤ እነዚህንም ነገሮች በሥራ ላይ በማዋል ሁለንተናህን ለእነርሱ ስጥ።


ቤተ ክርስቲያንን በደንብ የሚያስተዳድሩ፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙ ሽማግሌዎች እጥፍ ክብር ይገባቸዋል፤


ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ካልመሰከሩበት በቀር በቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ ላይ የሚቀርበውን ክስ አትቀበል።


የእምነትን መልካም ጦርነት ተዋጋ፤ አንተ ወደ እርሱ በተጠራህ ጊዜ በብዙ ምስክሮች ፊት ትክክለኛ ምስክርነትን የሰጠኸውን ዘለዓለማዊውን ሕይወት ያዝ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios