Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 19:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እርሱ ከመሄዱ በፊት ከአገልጋዮቹ ዐሥሩን ጠርቶ ለእያንዳንዱ ዐሥር ምናን ሰጣቸውና ‘ተመልሼ እስክመጣ ድረስ በዚህ ገንዘብ ነግዱ’ አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከባሮቹም መካከል ዐሥሩን ወደ ራሱ ጠርቶ ዐሥር ምናን ሰጣቸውና ‘ተመልሼ እስክመጣ ድረስ በዚህ ገንዘብ ነግዱበት’ አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ዐሥር አገልጋዮችንም ጠርቶ ዐሥር ምናን ሰጣቸውና ‘እስክመጣ ድረስ ነግዱ፤’ አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ዐሥ​ሩን አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ጠርቶ ዐሥር ምናን ሰጣ​ቸ​ውና፦ እን​ግ​ዲህ እስ​ክ​መ​ለስ ድረስ ነግዱ አላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 አሥር ባሪያዎችንም ጠርቶ አሥር ምናን ሰጣቸውና፦ እስክመጣ ድረስ ነግዱ አላቸው።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 19:13
15 Referencias Cruzadas  

እኔን ማገልገል የሚፈልግ ይከተለኝ፤ እኔ ባለሁበት አገልጋዬ በዚያ ይሆናል፤ የሚያገለግለኝንም አብ ያከብረዋል።”


የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና ሐዋርያ ከሆነው ከስምዖን ጴጥሮስ፥ ከአምላካችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኘው ጽድቅ አማካይነት እኛ እንዳገኘነው እምነት ያለ የከበረ እምነት ላገኛችሁት፤


በዓለም ሁሉ ለተበተኑ ለዐሥራ ሁለቱ ነገዶች የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ከሆነው ከያዕቆብ የተላከ መልእክት፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን።


ታዲያ፥ እኔ የምፈልገው ሰው እንዲያመሰግነኝ ነውን? ወይስ እግዚአብሔር እንዲያመሰግነኝ? ወይስ ሰውን ደስ ለማሰኘት የምፈልግ መስሎአችሁ ይሆን? ሰዎችን ለማስደሰት የምፈልግ ብሆን ኖሮ የክርስቶስ አገልጋይ ባልሆንኩም ነበር።


አምስት መክሊት የተቀበለው ወዲያውኑ ሄዶ ነገደበትና ሌላ አምስት መክሊት አተረፈ።


አምስት መክሊት የተቀበለው አገልጋይ ወደ ጌታው መጣና አምስት መክሊት አቅርቦ ‘ጌታ ሆይ! አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ! ሌላ አምስት መክሊት አትርፌአለሁ!’ አለ።


ሁለት መክሊት የተቀበለው ቀርቦ ‘ጌታ ሆይ! ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ ሌላ ሁለት መክሊት አትርፌአለሁ!’ አለ።


አንድ መክሊት የተቀበለውም ቀርቦ፥ ‘ጌታ ሆይ! ካልዘራህበት የምታጭድ፥ ካልበተንክበት የምትሰበስብ፥ ጨካኝ ሰው መሆንክን ዐውቃለሁ፤


ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “የንጉሥነትን ሥልጣን ተቀብሎ ለመመለስ ወደ ሩቅ አገር የሄደ አንድ መኰንን ነበረ፤


የአገሩ ሰዎች ግን ይጠሉት ስለ ነበር፥ ይህ ሰው በእኛ ላይ እንዲነግሥ አንፈልግም ሲሉ እርሱ ከሄደ በኋላ መልእክተኛ ላኩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios