2 ሳሙኤል 5:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍልስጥኤማውያን በሸሹ ጊዜ ጣዖቶቻቸውን ጥለው ሄዱ፤ ዳዊትና ተከታዮቹም ማርከው ወሰዱአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍልስጥኤማውያንም ጣዖቶቻቸውን ትተው ሸሽተው ስለ ነበር፣ ዳዊትና ሰዎቹ ወስደው አቃጠሏቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍልስጥኤማውያንም ጣዖቶቻቸውን ትተው ሸሹ፤ ዳዊትና ሰዎቹም ወሰዱአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጣዖቶቻቸውንም በዚያ ተዉ፤ ዳዊትና ሰዎቹም ወሰዱአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጣዖቶቻቸውንም በዚያ ተዉ፥ ዳዊትና ሰዎቹም ወሰዱአቸው። |
በግብጽ የጣዖትን ቤተ መቅደሶች ያቃጥላል፤ ጣዖቶቹን ይማርካል፤ እረኛ ለምዱን እንደሚደርብ ግብጽን በግዛቱ ላይ ደርቦ ምንም ጒዳት ሳይደርስበት በድል አድራጊነት ይወጣል።
“የሞአብ ሕዝብ ሆይ! በኀይላችሁና በሀብታችሁ ብዛት ተማምናችሁ ነበር፤ አሁን ግን እነሆ እናንተ ራሳችሁ እንኳ ትማረካላችሁ፤ ከሞሽ ተብሎ የሚጠራው ጣዖት ከልዑላን መሳፍንትና ከካህናቱ ጋር ተማርኮ ይወሰዳል።
የአማልክታቸውንም ምስሎች ከወርቅና ከብር ዕቃዎች ጋር ማርኮ ወደ ግብጽ ይወስዳል፤ ለጥቂት ዓመቶችም የግብጹ ንጉሥ የሶርያን ንጉሥ በጦርነት ለማጥቃት አይነሣም።
ጣዖቶቻቸውን በእሳት አቃጥል፤ በእነርሱ ላይ የተለበጠውን ብር ወይም ወርቅ የራስህ ንብረት አድርገህ ለመውሰድ ልብህ አይመኝ፤ ይህን ብታደርግ ወጥመድ ይሆንብሃል፤ እግዚአብሔርም አምልኮ ጣዖትን ስለሚጠላ ብርቱ ጥፋትን ያስከትልብሃል።
ነገር ግን በእነርሱ ላይ የምታደርጉት እንደዚህ ነው፦ መሠዊያዎቻቸውን አፍርሱ፤ ከድንጋይ የተሠሩ የጣዖት ማምለኪያ ዐምዶቻቸውንም እያንከታከታችሁ ጣሉ፤ አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስል ሰባብሩ፤ ጣዖቶቻቸውንም በእሳት አቃጥሉ፤