ቀስት በደመናዎች ላይ በሚታይበት ጊዜ ተመልክቼ በእኔና በምድር ላይ ባሉት ሕይወት ባላቸው ፍጥረቶች መካከል ያለውን ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ።”
2 ሳሙኤል 23:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሁሉም ነገር የተመቻቸና አስተማማኝ፥ ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ከእኔ ጋር ስለ ገባ፥ በውኑ ቤቴ ለእግዚአብሔር ታማኝ አይደለም? ርዳታዬና ፍላጎቴስ ሁሉ እንዲሟላ አያደርግምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የእኔስ ቤት በአምላክ ዘንድ ትክክል አይደለምን? ሁሉንም ነገር አዘጋጅቶና ጠብቆ፣ ከእኔ ጋራ ዘላለማዊ ኪዳን ያደረገ አይደለምን? ድነቴን ከፍጻሜ የሚያደርሰው፣ መሻቴን ሁሉ የሚሰጠኝ እርሱ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁሉንም ነገር አዘጋጅቶና ጠብቆ፥ ከእኔ ጋር ዘላለማዊ ኪዳን ያደረገ፥ መዳኔን ከፍጻሜ የሚያደርሰው፥ መሻቴን ሁሉ የሚሰጠኝ እርሱ አይደለምን? በውኑ ቤቴ በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲህ አይደለምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኑ ቤቴ በኀያሉ ዘንድ እንዲሁ አይደለምን? ከእኔም ጋር በዘመኑ ሁሉ የተዘጋጀና የተጠበቀ፥ የዘለዓለም ቃል ኪዳን አድርጎአል፤ መድኀኒቴም ፈቃዴም ሁሉ ይህ ነውና። ዐመፀኛም አይበቅልምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ቤቴ በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲሁ አይደለምን? ከእኔም ጋር በሁሉ ነገር ቅንና ጽኑ የሆነውን የዘላለም ቃል ኪዳን አድርጎአል፥ መድኃኒቴንና ፈቃዴን ሁሉ ያበቅላል። |
ቀስት በደመናዎች ላይ በሚታይበት ጊዜ ተመልክቼ በእኔና በምድር ላይ ባሉት ሕይወት ባላቸው ፍጥረቶች መካከል ያለውን ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ።”
አገልጋዮቹንም “አምኖን ብዙ ጠጥቶ መስከሩን ተመልከቱ፤ እኔም ትእዛዝ በምሰጣችሁ ጊዜ ግደሉት፤ ይህን ትእዛዝ የሰጠኋችሁ እኔ ስለ ሆንኩ ከቶ አትፍሩ! ደፋሮች ሁኑ፤ ምንም አታመንቱ!” አላቸው።
ኢዮአብም “እኔ አሁን ከአንተ ጋር ጊዜ ማባከን አልፈልግም” አለውና ሦስት ጦሮችን ወስዶ አቤሴሎም በወርካው ዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ ገና በሕይወት ሳለ በደረቱ ተከለበት።
ዘመንህ ተፈጽሞ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በምታርፍበት ጊዜ ከአብራክህ የሚወጣውን ልጅህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ፤ የእርሱንም መንግሥት አጸናለሁ።
ከዚህ በኋላ ንጉሥ ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ተቀምጦ እንዲህ ሲል ጸለየ፦ “እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ እስከዚህ ድረስ ያደረስከኝ፤ እኔ ማን ነኝ? ቤተሰቤስ ምንድን ነው?
ከአቤሴሎም በኋላ ከዳዊትና ከሐጊት የተወለደ በሕይወት ያለ ተከታይ ልጅ አዶንያስ ነበር፤ እርሱም እጅግ መልከ ቀና ነበር፤ ዳዊት ስለማናቸውም ነገር ምክርና ተግሣጽ ሰጥቶት አያውቅም ነበር፤ ከዚህም የተነሣ አዶንያስ ለመንገሥ ፈለገ፤ ይህንንም ፍላጎቱን ለማሟላት ሠረገሎችን፥ ፈረሶችንና ኀምሳ ጋሻ ጃግሬዎችን አዘጋጀ።
አገልጋዬ ዳዊት እንዳደረገው በፍጹም ልብህ ብትታዘዘኝ፥ በሕጎቼና በትእዛዞቼ ጸንተህ ብትኖር፥ በእኔ ፊት ሞገስ ብታገኝ፥ እኔ ዘወትር ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ በእስራኤል ላይ እንድትነግሥም አደርግሃለሁ፤ ለዳዊት ባደረግሁት ዐይነት ዘሮችህ ከአንተ በኋላ እንደሚነግሡ አረጋግጥልሃለሁ።
ወጣቶቹም በሰጡት ምክር መሠረት “አባቴ በእናንተ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፤ እኔ ደግሞ ይኸው የአገዛዝ ቀንበር ይበልጥ እንዲከብድባችሁ አደርጋለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ይገርፋችሁ ነበር፤ እኔ ግን እንደ ጊንጥ በሚናደፍ ጅራፍ በመግረፍ አሠቃያችኋለሁ!” ሲል መለሰላቸው።
እግዚአብሔርን አንድ ነገር እለምነዋለሁ፤ የምለምነውም፦ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ የእግዚአብሔርን አስደናቂነት እንድመለከትና በቤተ መቅደሱም መጸለይ እንድችል ነው።
በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር በምድሪቱ ያለውን የተክልና የዛፍ ቅርንጫፍ ልምላሜ የተዋበና የተከበረ ያደርገዋል፤ ከእስራኤል ወገን ከጥፋት የተረፉት ሁሉ ምድሪቱ በምታስገኘው ሰብል ደስታና ኲራት ይሰማቸዋል።
ተራራዎችና ኰረብቶች ሊናወጡና ሊፈርሱ ይችላሉ፤ እኔ ለአንቺ ያለኝ ፍቅር ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፤ የሰላምንም የተስፋ ቃሌን ለዘለዓለም እጠብቅልሻለሁ፤” ይላል ለአንቺ የሚራራ እግዚአብሔር።
“ጆሮአችሁን አዘንብላችሁ ወደ እኔ ቅረቡ፤ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ቃሌን አድምጡ፤ ዳዊትን እንደ ወደድኩት እናንተን በታማኝነት ለመውደድ ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን እገባለሁ።
እኔ እግዚአብሔር ፍትሕን እወዳለሁ፤ ቅሚያንና ክፉ ድርጊትን እጠላለሁ፤ እኔ ተገቢ ዋጋቸውን እሰጣቸዋለሁ፤ ከእነርሱም ጋር ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን እገባለሁ።
ከእነርሱ ጋር የዘለዓለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ ለእነርሱ መልካም ነገር ከማድረግም አላቋርጥም፤ በእውነት እንዲፈሩኝ አደርጋለሁ። ከዚያም በኋላ ፊታቸውን ከእኔ ወደ ሌላ አይመልሱም።
ከእነርሱ ጋር የሰላም ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ ያም ቃል ኪዳን ዘለዓለማዊ ነው፤ እነርሱንም እንደገና መሥርቼ የሕዝቡን ቊጥር አበዛለሁ፤ ቤተ መቅደሴንም ለዘለዓለም ጸንቶ በሚቈይበት ስፍራ በምድራቸው አኖራለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ፈራርሶ እንደ ወደቀ ቤት የነበረውን የዳዊትን ሥርወ መንግሥት መልሼ የማቋቊምበት ጊዜ ይመጣል፤ ቅጽሩን እጠግናለሁ፤ ፍርስራሹንም አድሳለሁ፤ በቀድሞ ዘመን እንደ ነበረውም አድርጌ እሠራዋለሁ፤
መበስበስ እንዳይደርስበት እግዚአብሔር ከሞት እንዳስነሣው ለማስረዳት፥ ‘ቅዱሱን የታመነ በረከትን ለዳዊት የተሰጠውን ተስፋ እሰጣችኋለሁ’ ብሎ ተናግሮአል።
ለእኔም እንደ ልቤና እንደ ሐሳቤ የሚያደርግ አንድ ታማኝ ካህን አስነሣለሁ፤ ለእርሱም የጸና ዘር እመሠርትለታለሁ፤ እኔ በቀባሁትም ንጉሥ ፊት ይመላለሳል።
ጌታዬ፥ አንተ የእግዚአብሔርን ጦርነት እየተዋጋህ ነው፤ በምትኖርበትም ዘመን ሁሉ ምንም ዐይነት ክፉ ነገር ማድረግን ስለማትፈልግ ስለ ፈጸምኩት በደል እባክህ ይቅር በለኝ፤ እግዚአብሔር አንተንና ዘሮችህን ለዘለዓለም ያነግሣል፤