2 ሳሙኤል 22:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤ እርሱም ከጠላቶቼ ያድነኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤ ከጠላቶቼም እድናለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምስጋና የሚገባውን ጌታን እጠራለሁ፤ ከጠላቶቼም እድናለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤ ከጠላቶቼም እድናለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፥ ከጠላቶቼም እድናለሁ። |
ኢያሱ፥ ቃድሚኤል፥ ባኒ፥ ሐሸባንያ፥ ሼሬብያ፥ ሆዲያ፥ ሸባንያና ፐታሕያ ተብለው የሚጠሩት ሌዋውያን፦ “ተነሥታችሁ በመቆም ዘለዓለማዊውን አምላካችሁን እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ከምስጋናና ከበረከት ሁሉ በላይ፥ ከፍ ከፍ ይበል! በሉ” አሉአቸው።
“ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ ሁሉን ነገር ስለ ፈጠርክ ሁሉም ነገር የተፈጠረውና የሚኖረው (ሕይወትን ያገኘው) በአንተ ፈቃድ ስለ ሆነ ገናናነት፥ ክብርና ኀይልም ለአንተ ይገባል” ይሉ ነበር።