አቤሴሎም በኢዮአብ ምትክ ዐማሣ ተብሎ የሚጠራውን ሰው የጦር አዛዥ አድርጎ ሾመ፤ ዐማሣ የእስራኤላዊው የዬቴር ልጅ ነበር፤ እናቱም አቢጌል ተብላ የምትጠራ የናሐሽ ልጅ ስትሆን ለኢዮአብ እናት ለጸሩያ እኅት ነበረች። ዜና መ. 2፥17
2 ሳሙኤል 20:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዐማሳ ሬሳ በደም እንደ ተበከለ በመንገዱ መካከል ተዘርሮ ነበር፤ ያም ሰው የኢዮአብ ወታደር ሁሉ ቆሞ ሲመለከት አይቶ ሬሳውን በመጐተት ወደ እርሻ ወሰደውና በልብስ ሸፈነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ የአሜሳይ ሬሳ በደም ተጨማልቆ በመንገዱ መካከል ወድቆ ነበር፤ በዚያ የሚያልፈው ሰራዊት ሁሉ መቆሙን ያ ሰው አየ፤ ወደ ሬሳው የደረሰው ሰራዊት ሁሉ መቆሙን በተረዳ ጊዜም፣ የአሜሳይን ሬሳ ከመንገድ ወደ ዕርሻ ፈቀቅ አድርጎ ልብስ ጣል አደረገበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህን ጊዜ የአማሳይ ሬሳ በደም ተጨማልቆ በመንገዱ መካከል ወድቆ ነበር፤ በዚያ የሚያልፈው ሠራዊት ሁሉ መቆሙን ያ ሰው አየ፤ ወደ ሬሳው የደረሰው ሠራዊት ሁሉ መቆሙን በተረዳ ጊዜም፥ የአማሳይን ሬሳ ከመንገድ ወደ እርሻ ፈቀቅ አድርጎ በልብስ ሸፈነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሜሳይም በደም ተነክሮ በመንገድ መካከል ወድቆ ነበር፤ ያም ሰው ወደ እርሱ የሚመጣ ሁሉ ሲቆም አይቶአልና ሕዝቡ ሁሉ እንደ ቆመ ባየ ጊዜ አሜሳይን ከመንገድ ላይ ወደ እርሻ ውስጥ ፈቀቅ አደረገው፤ በልብስም ከደነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሜሳይም በመንገድ መካከል ወድቆ በደሙ ላይ ይንከባለል ነበር፥ ያም ሰው ወደ እርሱ የሚመጣ ሁሉ ሲቆም አይቶአልና ሕዝቡ ሁሉ እንደ ቆመ ባየ ጊዜ አሜሳይን ከመንገድ ላይ ወደ እርሻ ውስጥ ፈቀቅ አደረገው፥ በልብስም ከደነው። |
አቤሴሎም በኢዮአብ ምትክ ዐማሣ ተብሎ የሚጠራውን ሰው የጦር አዛዥ አድርጎ ሾመ፤ ዐማሣ የእስራኤላዊው የዬቴር ልጅ ነበር፤ እናቱም አቢጌል ተብላ የምትጠራ የናሐሽ ልጅ ስትሆን ለኢዮአብ እናት ለጸሩያ እኅት ነበረች። ዜና መ. 2፥17
ዐሣሄል ግን አሁንም ማሳደዱን ሊተው አልፈቀደም፤ ስለዚህ አበኔር ጦሩን ወደ ኋላው ወርውሮ ሆዱ ላይ ሲሽጥበት ጫፉ ዘልቆ በጀርባው ወጣ፤ ዐሣሄልም መሬት ላይ ወድቆ ሞተ፤ ሬሳው በተጋደመበት ስፍራ የሚያልፍ ሰው ሁሉ በአጠገቡ ቆሞ ይመለከተው ነበር።
ከኢዮአብ ወታደሮች አንዱ በዐማሳ ሬሳ አጠገብ ቆሞ “ኢዮአብንና ዳዊትን የምትከተሉ ሁሉ ኢዮአብን ተከተሉ!” ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ።
አምላክ ሆይ! አንተ ግን ክፉዎችን ወደ ጥልቅ ጒድጓድ ትጥላቸዋለህ፤ እነዚያ ነፍሰ ገዳዮችና ከዳተኞች ግማሽ ዕድሜአቸውን እንኳ አይኖሩም፤ እኔ ግን በአንተ እተማመናለሁ።