2 ሳሙኤል 19:42 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳም ሰዎች “እኛ ይህን ያደረግነው ንጉሡ የእኛ ወገን ስለ ሆነ ብቻ ነው፤ ታዲያ፥ እናንተስ በዚህ ነገር ስለምን ትቈጣላችሁ? እርሱ ለምግባችን ምንም የከፈለን ነገር የለም፤ ሌላም ምንም ነገር አልሰጠንም” ሲሉ መለሱላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳም ሰዎች ሁሉ፣ ለእስራኤል ሰዎች፣ “ይህን ያደረግነው ንጉሡ የቅርብ ዘመዳችን ስለ ሆነ ነው፤ ታዲያ ይህ እናንተን የሚያስቈጣ ነው? እኛ ከንጉሡ ተቀብለን አንዳች በልተናልን? ለራሳችንስ ምን የወሰድነው ነገር አለ?” አሏቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወዲያውም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ መጥተው፥ “ወንድሞቻችን የይሁዳ ሰዎች ንጉሡን በሹልክታ ለብቻቸው ይዘው እርሱንና ቤተሰቡን ከተከታዮቹ ጋር ዮርዳኖስን ለምን አሻገሩ?” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳም ሰዎች ሁሉ ለእስራኤል ሰዎች መልሰው፥ “ንጉሡ ለእኛ ቅርባችን ነው፤ ስለምን በዚህ ነገር ትቈጣላችሁ? በውኑ ከንጉሡ አንዳች በልተናልን? ወይስ እርሱ በረከት ሰጥቶናልን? ወይስ ጭፍራ አድርጎ ሾመንን?” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይሁዳም ሰዎች ሁሉ ለእስራኤል ሰዎች መልሰው፦ ንጉሡ ለእኛ ቅርባችን ነው፥ ስለ ምን በዚህ ነገር ትቆጣላችሁ? በውኑ ከንጉሡ አንዳች በልተናልን? ወይስ እርሱ በረከት ሰጥቶናልን? አሉ። |
እስራኤላውያንም “እርሱ የእናንተ ወገን ቢሆንም እንኳ እናንተ ከምትፈልጉት ይበልጥ እኛ እንፈልገዋለን፤ ከመንግሥቱ ዐሥሩ እጅ የሚገባው ለእኛው ነው፤ እናንተ እኛን የምትንቁት ስለምንድን ነው? ንጉሡን ስለ መመለስ በመጀመሪያ ጥያቄ ያቀረብነው እኛ መሆናችንን ልትዘነጉ አይገባም!” አሉአቸው። ነገር ግን ከእስራኤል ሰዎች ይልቅ የይሁዳ ሰዎች ዳዊትን የራሳቸው ለማድረግ በብርቱ ተከራከሩ።
ከዚህ በኋላ የይሁዳ ሰዎች ወደ ኬብሮን መጡ፤ ዳዊትንም ቀብተው የይሁዳ ንጉሥ አደረጉት። ዳዊት ገለዓዳውያን የሆኑ የያቤሽ ሰዎች ሳኦልን እንደ ቀበሩት በሰማ ጊዜ፥
ከዚህ በኋላ የእስራኤል ነገዶች ሁሉ በኬብሮን ወደነበረው ወደ ዳዊት ሄደው እንዲህ አሉት፦ “እነሆ እኛ የአጥንትህ ፍላጭ፥ የሥጋህ ቊራጭ የሆንን ወገኖችህ ነን።
ከዚህ በኋላ የኤፍሬም ሰዎች ጌዴዎንን “ምድያማውያንን ለመውጋት ስትሄድ እኛን ለምን አልጠራኸንም? በእኛ ላይ ለምን እንዲህ አደረግህ?” ሲሉ በምሬት ወቀሱት።