Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 8:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ከዚህ በኋላ የኤፍሬም ሰዎች ጌዴዎንን “ምድያማውያንን ለመውጋት ስትሄድ እኛን ለምን አልጠራኸንም? በእኛ ላይ ለምን እንዲህ አደረግህ?” ሲሉ በምሬት ወቀሱት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በዚህ ጊዜ የኤፍሬም ሰዎች፣ “ምድያማውያንን ለመውጋት ስትሄድ ለምን አልጠራኸንም? ለምንስ እንዲህ ያለ ነገር አደረግህ?” በማለት ጌዴዎንን እጅግ ነቀፉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በዚያን ጊዜ የኤፍሬም ሰዎች፥ “ምድያማውያንን ለመውጋት ስትሄድ ለምን አልጠራኸንም? ለምንስ እንዲህ ያለ ነገር አደረግህ?” በማለት ጌዴዎንን እጅግ ነቀፉት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የኤ​ፍ​ሬም ሰዎ​ችም፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ምን​ድን ነው? ምድ​ያ​ምን ለመ​ዋ​ጋት በወ​ጣህ ጊዜ ለምን አል​ጠ​ራ​ኸ​ንም?” አሉት። ጽኑ ጥልም ተጣ​ሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የኤፍሬም ሰዎች፦ ይህ ያደረግህብን ምንድር ነው? ምድያምን ለመዋጋት በወጣህ ጊዜ ለምን አልጠራኸንም? አሉት። ጽኑ ጥልም ተጣሉት።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 8:1
9 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን ሁሉ ወደ ንጉሡ ቀርበው “ንጉሥ ሆይ! ወንድሞቻችን የይሁዳ ሰዎች አንተን ወስደው የራሳቸው ለማድረግ፥ እንዲሁም አንተንና ቤተሰብህን፥ ተከታዮችህንም ሁሉ አጅበው የዮርዳኖስን ወንዝ ለማሻገር መብት እንዳላቸው ስለምን ያስባሉ?” ሲሉ ጠየቁት።


የይሁዳም ሰዎች “እኛ ይህን ያደረግነው ንጉሡ የእኛ ወገን ስለ ሆነ ብቻ ነው፤ ታዲያ፥ እናንተስ በዚህ ነገር ስለምን ትቈጣላችሁ? እርሱ ለምግባችን ምንም የከፈለን ነገር የለም፤ ሌላም ምንም ነገር አልሰጠንም” ሲሉ መለሱላቸው።


ቊጣ ሞኝን ይገድለዋል፤ ቅናትም ሰውን ያጠፋል።


ልዝብ አነጋገር ቊጣን ያስታግሣል፤ የቊጣ አነጋገር ግን ቊጣን ያባብሳል።


ደግሞም ሰዎች የተመኙትን ለማግኘት ተግተው በመሥራት ምን ያኽል እንደሚደክሙ ተመለከትኩ፤ ይህንንም የሚያደርጉት በባልንጀሮቻቸው ላይ በመቅናት መሆኑን ተረዳሁ፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ስለ ሆነ ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ነው።


የኤፍሬም ነገድ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ከፍ ብሎ በነበረበት ዘመን ሲናገር የሚሰሙት ሁሉ ይንቀጠቀጡ ነበር፤ በኋላ ግን ባዓል ለተባለ ጣዖት በመስገድ ኃጢአት ስለ ሠራ በሞት ተቀጣ።


እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፤ “እኔ ካደረግሁት እናንተ ያደረጋችኹት አይበልጥምን? የእኔ ጐሣ በሙሉ ከሠራው ሥራ የኤፍሬም ሰዎች የሠራችሁት ጥቂቱ ሥራ ይበልጣል። የኤፍሬም ወይን ቃርሚያ ከአቢዔዜር ወይን መከር አይሻልምን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos