አቤሴሎም በኢዮአብ ምትክ ዐማሣ ተብሎ የሚጠራውን ሰው የጦር አዛዥ አድርጎ ሾመ፤ ዐማሣ የእስራኤላዊው የዬቴር ልጅ ነበር፤ እናቱም አቢጌል ተብላ የምትጠራ የናሐሽ ልጅ ስትሆን ለኢዮአብ እናት ለጸሩያ እኅት ነበረች። ዜና መ. 2፥17
2 ሳሙኤል 17:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አቤሴሎምና ሠራዊቱም በገለዓድ ምድር ሰፈሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያንና አቤሴሎም በገለዓድ ምድር ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤላውያንና አቤሴሎም በገለዓድ ምድር ሰፈሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤልና አቤሴሎምም በገለዓድ ምድር ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልና አቤሴሎምም በገለዓድ ምድር ሰፈሩ። |
አቤሴሎም በኢዮአብ ምትክ ዐማሣ ተብሎ የሚጠራውን ሰው የጦር አዛዥ አድርጎ ሾመ፤ ዐማሣ የእስራኤላዊው የዬቴር ልጅ ነበር፤ እናቱም አቢጌል ተብላ የምትጠራ የናሐሽ ልጅ ስትሆን ለኢዮአብ እናት ለጸሩያ እኅት ነበረች። ዜና መ. 2፥17
ዳዊት ማሕናይም በደረሰ ጊዜ በዐሞን ግዛት ራባ ተብላ ከምትጠራው ከተማ የመጣውን የናዖስን ልጅ ሾቢን፥ ከሎደባር ከተማ የመጣውን የዓሚኤልን ልጅ ማኪርንና ከገለዓድ ግዛት ሮገሊም ተብላ ከምትጠራው ከተማ የመጣውን ባርዚላይን አገኘ።
ይህ የዮሴፍ በኲር ልጅ የነበረው የምናሴ ነገድ ድርሻ የሚከተለው ነው። የምናሴ በኲር ልጅ የገለዓድ አባት ማኪር የጦር ጀግና ስለ ነበረ ገለዓድና ባሳን በርስትነት ተሰጠው።