2 ሳሙኤል 15:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢታይ ግን ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ጌታዬ በሚኖርበት ቦታ ሁሉ፥ በሞትም ሆነ በሕይወት እኔ አገልጋይህ በዚያ እንደምገኝ በእግዚአብሔር ስም እንዲሁም በጌታዬ በንጉሡ ሕይወት እምላለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢታይ ግን፣ “ሕያው እግዚአብሔርን! እንዲሁም በጌታዬ በንጉሡ እምላለሁ፤ ሕይወትም ይሁን ሞት በየትም ቦታ ንጉሥ ጌታዬ የሚሆነውን ሁሉ አገልጋይህም እንደዚያው ይሆናል” ብሎ መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢታይ ግን፥ “በሕያው ጌታ ስም እምላለሁ! እንዲሁም በጌታዬ በንጉሡ እምላለሁ፤ ሕይወትም ይሁን ሞት በየትም ቦታ ንጉሥ ጌታዬ የሚሆነውን ሁሉ አገልጋይህም እንደዚያው እሆናለሁ” ብሎ መለሰለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤቲም ለንጉሡ መልሶ፥ “ሕያው እግዚአብሔርን! በጌታዬም በንጉሡ ሕይወት እምላለሁ! ጌታዬ ባለበት ስፍራ ሁሉ፥ በሞትም ቢሆን በሕይወትም፥ በዚያ ደግሞ እኔ አገልጋይህ እሆናለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢታይም ለንጉሡ መልሶ፦ ሕያው እግዚአብሔርን! በጌታዬም በንጉሡ ሕይወት እምላለሁ! በእውነት ጌታዬ ባለበት ስፍራ ሁሉ፥ በሞትም ቢሆን በሕይወትም፥ በዚያ ደግሞ እኔ ባሪያህ እሆናለሁ አለው። |
በመንገድም ሳሉ ኤልያስ ኤልሳዕን “እነሆ፥ አንተ በዚህ ቈይ፤ እኔ ወደ ቤትኤል እንድሄድ እግዚአብሔር አዞኛል” አለው። ኤልሳዕ ግን “እኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ ከቶ ከአንተ አልለይም” ሲል መለሰለት፤ ስለዚህም አብረው ወደ ቤትኤል ሄዱ።
ከዚህም በኋላ ኤልያስ ኤልሳዕን፥ “እነሆ! አንተ በዚህ ቈይ፤ እኔ ወደ ኢያሪኮ እንድሄድ እግዚአብሔር አዞኛል” አለው። ኤልሳዕ ግን “እኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ! ከቶ ከአንተ አልለይም!” ሲል መለሰለት፤ ስለዚህም አብረው ወደ ኢያሪኮ ሄዱ።
ከዚህም በኋላ ኤልያስ ኤልሳዕን፥ “እነሆ! አንተ በዚህ ቈይ፤ እኔ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ እንድሄድ እግዚአብሔር አዞኛል” አለው። ኤልሳዕ ግን “እኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ! ከቶ ከአንተ አልለይም!” ሲል መለሰለት፤ ስለዚህም አብረው ጒዞአቸውን ቀጠሉ።
የልጁ እናት ግን ኤልሳዕን “በምተማመንበት በሕያው እግዚአብሔር ስምና በነፍስህ እምላለሁ፤ ከቶ አንተን ትቼ አልሄድም!” አለችው፤ ስለዚህ እርስዋን ተከትሎ ለመሄድ ተነሣ፤
እርሱም ሄዶ እግዚአብሔር ጸጋውን ለሕዝቡ እንዴት እንደ ሰጠ ባየ ጊዜ ደስ አለው፤ ሁሉም በሙሉ ልብ ጸንተው ለጌታ ታማኞች ሆነው እንዲኖሩም መከራቸው።
ጳውሎስ ግን “እንደዚህ እያለቀሳችሁ ስለምን ልቤን በሐዘን ትሰብሩታላችሁ? እኔ ስለ ጌታ ኢየሱስ ስም በኢየሩሳሌም ለመታሰር ብቻ ሳይሆን ለመሞትም ዝግጁ ነኝ” ሲል መለሰ።
ይህንንም የምለው በእናንተ ላይ ለመፍረድ አይደለም። ከዚህ በፊት እንደ ነገርኳችሁ እናንተ በልባችን ውስጥ ናችሁ፤ ስለዚህ በሕይወትም ሆነ በሞት ሁልጊዜ ከእናንተ አንለይም።
ዳዊት ግን “አባትህ አንተ እኔን ምን ያኽል እንደምትወደኝ በደንብ ያውቃል፤ ስለዚህም ዕቅዱን አንተ እንድታውቅበት ላለማድረግ ወስኖአል፤ ይህንንም የሚያደርገው አንተ ይህን ብታውቅ በብርቱ እንደምታዝን ስለሚያውቅ ነው፤ በሕያው እግዚአብሔር ስምና በነፍስህ እምላለሁ፤ ከአሁን ወዲያ ወደ ሞት ለመድረስ የቀረችን አንዲት ዕርምጃ ብቻ ናት!” አለው።
የበቀል እርምጃ በመውሰድ ጠላቶችህን እንዳትገድል የጠበቀህ ራሱ እግዚአብሔር ነው፤ እነሆ፥ እኔ አሁን በሕያው እግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ፤ ጠላቶችህና አንተን ለመጒዳት የሚፈልጉ ሁሉ እንደ ናባል ቅጣታቸውን ይቀበሉ፤