2 ሳሙኤል 1:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም “ታዲያ እግዚአብሔር መርጦ የቀባውን ንጉሥ ለመግደል እንዴት ደፈርክ?” ሲል ጠየቀው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም፣ “ታዲያ እግዚአብሔር የቀባውን ለማጥፋት እጅህን ስታነሣ እንዴት አልፈራህም?” ሲል ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም፥ “ታዲያ ጌታ የቀባውን ለማጥፋት እጅህን ስታነሣ እንዴት አልፈራህም?” ሲል ጠየቀው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም፥ “ትገድለው ዘንድ እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጅህን ስትዘረጋ እንዴት አልፈራህም?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም፦ እግዚአብሔር የቀባውን ለመግደል እጅህን ስትዘረጋ ለምን አልፈራህም? አለው። |
ስለዚህም እኔ ከእርሱ ጋር ቃል ለቃል በግልጥ እነጋገራለሁ እንጂ ስውር በሆነ አነጋገር አልናገረውም፤ የእኔን የእግዚአብሔርን መልክ ያያል፤ ታዲያ፥ እናንተ በአገልጋዬ በሙሴ ላይ ትናገሩ ዘንድ እንዴት ደፈራችሁ?”
በተለይም እነዚያን ርኩስ የሆነውን የሥጋ ፍትወታቸውን የሚከተሉትንና የእግዚአብሔርን ሥልጣን የሚንቁትን ለፍርድ ጠብቆ ያቈያቸዋል። እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ደፋሮችና ትዕቢተኞች ስለ ሆኑ የሰማይ ሥልጣናትን ሲሳደቡ አይፈሩም።
ሳሙኤል የወይራ ዘይት መያዣውን ቀንድ ወስዶ በሳኦል ራስ ላይ አፈሰሰው፤ ሳመውም። ከዚያም በኋላ “እግዚአብሔር በሕዝቡ በእስራኤል ላይ መሪ እንድትሆን ቀባህ፤ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ነግሠህ በዙሪያቸው ካሉ ጠላቶች ታድናቸዋለህ እግዚአብሔር በርስቱ ላይ የሾመህ ለመሆኑ ይህ ማስረጃ ነው፤
እነሆ አሁን በፊታችሁ ቆሜአለሁ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ንጉሥ ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወስጄአለሁ? የማንንስ አህያ ወስጄአለሁ? ማንንስ አታልዬአለሁ? ማንንስ ጨቊኜአለሁ? ፍርድን ለማዛባት ከማን ላይ ጉቦ ተቀብዬአለሁ? ከእነዚህ ሁሉ አንዱን አድርጌ ከሆነ የወሰድኩትን ለመመለስ ዝግጁ ነኝ።”
አባቴ ሆይ! እነሆ፥ ከካባህ ላይ ቈርጬ የያዝኩትን ጨርቅ ተመልከት! ታዲያ እኮ ልገድልህ እችል ነበር፤ ነገር ግን ይህን በማድረግ ፈንታ የልብስህን ጫፍ ቈረጥሁ፤ በአንተ ላይ ለማመፅም ሆነ ወይም በአንተ ላይ ጒዳት ላደርስብህ አለመፈለጌን በዚህ መረዳት ትችላለህ፤ አንተ ግን ምንም ነገር ሳላደርግና ሳልበድልህ እኔን ለመግደል ትከታተለኛለህ።
ስለዚህም ተከታዮቹን “እግዚአብሔር ቀብቶ ባነገሠው በጌታዬ ላይ እጄን ከማንሣት እግዚአብሔር ይጠብቀኝ! እርሱ እግዚአብሔር የመረጠው ንጉሥ ስለ ሆነ እኔ በእርሱ ላይ ምንም ዐይነት ጒዳት ላደርስበት አይገባኝም!” አላቸው።
ጋሻጃግሬው የነበረውንም ወጣት “እነዚህ ያልተገረዙ እኔን ወግተው በመሳለቅ መጫወቻ እንዳያደርጉኝ አንተ ራስህ ሰይፍህን መዘህ ግደለኝ” አለው፤ ወጣቱ ግን ፈርቶ አልገደለውም፤ ስለዚህም ሳኦል ራሱ የገዛ ሰይፉን ወስዶ በስለቱ ላይ ወደቀበት።