2 ጴጥሮስ 3:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ እነዚህ ሁሉ ነገሮች በዚህ ሁኔታ የሚጠፉ ከሆነ፥ ታዲያ፥ እናንተ በቅድስናና እግዚአብሔርን በማምለክ መኖር እንዴት አይገባችሁም? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ሁሉም ነገር በዚህ ሁኔታ የሚጠፋ ከሆነ፣ እናንተ እንዴት ዐይነት ሰዎች ልትሆኑ ይገባችኋል? አዎን፣ በቅድስናና በእውነተኛ መንፈሳዊነት ልትኖሩ ይገባችኋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ እነዚህ ሁሉ ነገሮች በዚህ ሁኔታ የሚጠፉ ከሆነ፥ በቅዱስ ኑሮ እግዚአብሔርንም በመምሰል መኖር አይገባችሁም? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህ ሁሉ እንዲህ የሚቀልጥ ከሆነ፥ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት እየጠበቃችሁና እያስቸኰላችሁ በቅዱስ ኑሮ እግዚአብሔርንም በመምሰል እንደ ምን ልትሆኑ ይገባችኋል? ስለዚያ ቀን ሰማያት ተቃጥለው ይቀልጣሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይፈታል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ ሁሉ እንዲህ የሚቀልጥ ከሆነ፥ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት እየጠበቃችሁና እያስቸኰላችሁ፥ በቅዱስ ኑሮ እግዚአብሔርንም በመምሰል እንደ ምን ልትሆኑ ይገባችኋል? ስለዚያ ቀን ሰማያት ተቃጥለው ይቀልጣሉ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይፈታል፤ |
በመግቢያው በር ሆናችሁ ወዮ በሉ! በከተማው ውስጥ ሆናችሁ ኡኡ! በሉ፤ ከወታደሮቹ አንዱ እንኳ ወደ ኋላ የማይል ኀይለኛ ጠላት ከሰሜን ስለ መጣ ፍልስጥኤማውያን ሁሉ በፍርሃት ይርበድበዱ!
ፀሐይ፥ ጨረቃና ከዋክብት ሁሉ ይጠፋሉ፤ ሰማይም እንደ ብራና ተጠቅሎ ይወገዳል፤ ከዋክብትም እንደ ወይንና እንደ በለስ ዛፍ ቅጠል ይረግፋሉ።
እንግዲህ ከእንቅልፍ የምትነቁበት ሰዓት አሁን መድረሱን ዕወቁ፤ በፊት ካመንበት ጊዜ ይልቅ አሁን የምንድንበት ቀን ይበልጥ ወደ እኛ ቀርቦአል።
የምንመካበት ነገር ይህ ነው፤ ይህም እውነት መሆኑን ኅሊናችን ይመሰክርልናል፤ ከሌሎች ሰዎችና በተለይም ከእናንተ ጋር የነበረን ግንኙነት ከእግዚአብሔር ባገኘነው ቅድስናና ቅንነት የተመሠረተ ነው፤ ይህም የሆነው በእግዚአብሔር ጸጋ ነበር እንጂ በሰው ጥበብ አልነበረም።
እንግዲህ ከሁሉም በላይ ሕይወታችሁ የክርስቶስን ወንጌል የሚያስመሰግን ይሁን፤ ይህም እኔ መጥቼ ባያችሁም ወይም ከእናንተ ብርቅ በአንድ ዓላማ ጸንታችሁ መቆማችሁንና ወንጌልን በኅብረት ለማዳረስ መጋደላችሁን እሰማለሁ።
ወንጌላችንን ያበሠርንላችሁ በቃል ብቻ ሳይሆን በኀይልና በመንፈስ ቅዱስ፥ ስለ ወንጌልም እውነት እርግጠኞች በመሆን ነው፤ ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ ለእናንተ ስንል እንዴት እንደ ኖርን ታውቃላችሁ።
የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም እግዚአብሔር፦ “ሰው ሆኖ ተገለጠ፤ እውነተኛነቱ በመንፈስ ታወቀ፥ ለመላእክት ታየ፥ ለሕዝቦች ሁሉ ተሰበከ፥ በዓለም ያሉ ሰዎች አመኑበት፥ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ” የሚል ነው።
የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! አንተ ግን ከዚህ ሁሉ ሽሽ፤ ጽድቅን፥ መንፈሳዊነትን፥ እምነትን፥ ፍቅርን፥ በትዕግሥት መጽናትን፥ ገርነትን ተከታተል።
ከእውነተኛ እግዚአብሔርን የማምለክ ትምህርት ጋር ተስማሚ የሆነውን፥ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ንጹሕ ቃል ትቶ የተለየ ትምህርት የሚያስተምር ማንም ሰው ቢኖር፤
“ያለኝ ይበቃኛል” ለሚል ሰው እግዚአብሔርን ማምለክ ትልቅ ጥቅም ያስገኝለታል። መንፈሳዊነትን ስለሚያተርፍበት ሃይማኖት የሀብት ምንጭ ነው።
ምናልባት “ክፉ አድራጊዎች ናቸው” ብለው ቢያሙአችሁም እንኳ እግዚአብሔር እኛን ለመጐብኘት በሚመጣበት ቀን አሕዛብ መልካም ሥራችሁን አይተው እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ በእነርሱ መካከል ስትኖሩ መልካም ጠባይ ይኑራችሁ።
የጌታ ቀን ግን እንደ ሌባ በድንገት ይመጣል፤ በዚያን ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፤ ፍጥረት ሁሉ በእሳት ተቃጥሎ ይጠፋል። ምድርና በእርስዋም ላይ ያለው ነገር ሁሉ ይቃጠላል፤
እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት በናፍቆት የምትጠባበቁና በቶሎም እንዲመጣ የምትሠሩ ሁኑ፤ በዚያን ቀን ሰማይ በእሳት ተቃጥሎ ይጠፋል፤ ፍጥረቶችም በእሳት ግለት ይቀልጣሉ፤